-
አዲሱ ዓለም—አንተም በዚያ ትገኝ ይሆን?መጠበቂያ ግንብ—2000 | ሚያዝያ 15
-
-
14, 15. በኢሳይያስ 65:21, 22 መሠረት ምን አርኪ የሆነ ሥራ ልትጠባበቅ ትችላለህ?
14 ኢሳይያስ ሆን ብሎ ኃጢአት የሚሠራ ሰው እንዴት እንደሚወገድ በመግለጹ ላይ ከማተኮር ይልቅ በአዲሱ ዓለም ውስጥ የሚኖረው የኑሮ ሁኔታ ምን እንደሚመስል ይገልጻል። በአዲሱ ዓለም ውስጥ እንደምትኖር አድርገህ አስብ። በመጀመሪያ በዓይነ ሕሊናህ የሚመጣው በመኖሪያህ ማለትም በቤትህ አካባቢ የሚኖረው ሁኔታ ነው። ኢሳይያስ በኢሳ 65 ቁጥር 21 እና 22 ላይ የሚገልጸው ይህንን ነው:- “ቤቶችንም ይሠራሉ፣ ይቀመጡባቸውማል፤ ወይኑንም ይተክላሉ ፍሬውንም ይበላሉ። ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፣ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፣ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋልና።”
-
-
አዲሱ ዓለም—አንተም በዚያ ትገኝ ይሆን?መጠበቂያ ግንብ—2000 | ሚያዝያ 15
-
-
16. አዲሱ ዓለም ዘላቂ እርካታ ያስገኛል ብለህ መጠበቅ የምትችለው ለምንድን ነው?
16 እንደነዚህ የመሰሉትን ዝርዝር ጉዳዮች ከማወቅ ይበልጥ የሚያስፈልገው የራስህ መኖሪያ ቤት እንደሚኖርህ ማወቁ ነው። ብዙ ደክመህ ከሠራህ በኋላ ሌላው ሰው ተጠቃሚ እንደሚሆንበት እንዳሁኑ ጊዜ አይሆንም። በተጨማሪም ኢሳይያስ 65:21 እንደምትተክልና ፍሬውንም እንደምትበላ ይናገራል። መላው ሁኔታ በዚህ ቃል እንደተጠቃለለ ግልጽ ነው። በራስህ ሥራ ማለትም በድካምህ ፍሬ ከፍተኛ እርካታ ታገኛለህ። “እንደ ዛፍ ዕድሜ” ረጅም በሆነው የሕይወት ዘመን ይህን ማከናወን ትችላለህ። በእርግጥም እንዲህ ያለው ሁኔታ ‘ሁሉ አዲስ ይሆናል’ ከሚለው መግለጫ ጋር የሚስማማ ነው!—መዝሙር 92:12-14
-