የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘በፈጠርሁት ለዘላለም ደስ ይበላችሁ’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 29. (ሀ) ታዛዥ የሆኑት የአምላክ ሕዝቦች የይሁዳ ምድር ቀድሞ ወደነበረችበት ሁኔታ ስትመለስ ምን አስደሳች ነገሮች ያገኛሉ? (ለ) ዛፍ ረጅም ዕድሜን ለማመልከት ተስማሚ ምሳሌ የሆነው ለምንድን ነው? (የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት።)

      29 ይሖዋ ቀድሞ ወደነበረችበት ሁኔታ በምትመለሰው የይሁዳ ምድር የሚኖረውን ሁኔታ እንዲህ ሲል መዘርዘሩን ቀጠለ:- “ቤቶችንም ይሠራሉ ይቀመጡባቸውማል፤ ወይኑንም ይተክላሉ ፍሬውንም ይበላሉ። ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፣ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፣ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋልና።” (ኢሳይያስ 65:21, 22) ታዛዥ የሆኑት የአምላክ ሕዝቦች ቤትም ሆነ ወይን አልባ ወደሆነውና ባድማ ሆኖ ወደቆየው የይሁዳ ምድር ከተመለሱ በኋላ ራሳቸው በሠሩት ቤት መኖርና ራሳቸው የተከሉትን ወይን መብላት መቻላቸው ከፍተኛ እርካታ ያስገኝላቸዋል። አምላክ የእጃቸውን ሥራ የሚባርከው ከመሆኑም በላይ በድካማቸው ፍሬ መደሰት የሚችሉበትን እንደ ዛፍ ያለ ረጅም ዕድሜ ይሰጣቸዋል።e

      30. በዛሬው ጊዜ የይሖዋ አገልጋዮች በምን አስደሳች ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ? በአዲሱ ዓለም ውስጥስ ምን አስደሳች ሁኔታ ይጠብቃቸዋል?

      30 ይህ ትንቢት በእኛም ዘመን ፍጻሜውን አግኝቷል። የይሖዋ ሕዝቦች በ1919 ከመንፈሳዊ ግዞት ነፃ በመውጣት ‘ምድራቸውን’ ወይም ሥራቸውንና አምልኳቸውን የሚያከናውኑበትን መስክ ቀድሞ ወደነበረበት ሁኔታ ለመመለስ ጥረት ማድረግ ጀመሩ። ጉባኤዎችን ከማቋቋማቸውም በላይ መንፈሳዊ ፍሬ አፍርተዋል። በመሆኑም የይሖዋ ሕዝቦች በአሁኑ ጊዜም እንኳ መንፈሳዊ ገነትና አምላክ የሚሰጠውን ሰላም አግኝተዋል። ይህ ሰላም በምድራዊቷ ገነት ውስጥም እንደሚኖር እርግጠኞች መሆን እንችላለን። ይሖዋ ታዛዥ ልብና እጅ ያላቸውን አምላኪዎቹን በመጠቀም በአዲሱ ዓለም ውስጥ ምን ሊያከናውን እንደሚችል ከወዲሁ ለመገመት አዳጋች ነው። የራስህን ቤት ሠርተህ መኖር መቻል ምንኛ የሚያስደስት ነገር ነው! በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ወቅት እርካታ የሚሰጥ ሥራ እንደ ልብ ይገኛል። የእጃችሁ ሥራ ዘወትር “መልካም” [NW ] ሲሆን ማየት ምንኛ የሚያስደስት ይሆናል! (መክብብ 3:​13) በእጃችን ሥራ በሚገባ ለመደሰት በቂ ጊዜ እናገኝ ይሆን? እንዴታ! ታማኝ ሰዎች የሚያገኙት ማብቂያ የሌለው ሕይወት “እንደ ዛፍ ዕድሜ” በሺህ ብሎም ከዚያ በሚበልጡ ዓመታት የሚቆጠር ይሆናል!

  • ‘በፈጠርሁት ለዘላለም ደስ ይበላችሁ’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • e ዛፎች በምድር ላይ ረጅም ዘመን ከሚኖሩ ሕያዋን ነገሮች መካከል የሚጠቀሱ በመሆኑ ረጅም ዕድሜን ለማመልከት ተስማሚ ምሳሌ ናቸው። ለምሳሌ ያህል የወይራ ዛፍ በመቶ ለሚቆጠሩ ዓመታት ፍሬ የሚያፈራ ሲሆን እስከ አንድ ሺህ ዓመት ድረስ ሊኖር ይችላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ