የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢየሱስ የተናገረው ስለ ገሃነመ እሳት ነበር?
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | ሰኔ 15
    • ይሁን እንጂ ኢየሱስ የተናገረውን ነገር በኢሳይያስ ትንቢት የመጨረሻ ቁጥር ላይ ካለው ሐሳብ ጋር እስቲ እናወዳድር።b ኢየሱስ፣ በኢሳይያስ ምዕራፍ 66 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ በተዘዋዋሪ መጥቀሱ እንደነበር ግልጽ ነው። በዚህ ጥቅስ ላይ ነቢዩ፣ “በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ወደነበረው የሄኖም ሸለቆ (ገሃነም)” ስለመውጣት መግለጹ ሳይሆን አይቀርም፤ “በዚህ ቦታ በአንድ ወቅት ሰዎች መሥዋዕት ይደረጉ የነበረ ሲሆን (ኤር. 7:31) ከጊዜ በኋላ ቦታው የከተማዋ ቆሻሻ መጣያ ሆኗል።” (ዘ ጄሮም ቢብሊካል ኮሜንታሪ) በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ኢሳይያስ 66:24 የሚናገረው ስለሚሠቃዩ ሰዎች ሳይሆን ስለ ሬሳ ነው። እንደማይሞቱ የተገለጹትም ትሎቹ እንጂ በሕይወት ያሉ ሰዎች ወይም የማይሞቱ ነፍሳት አይደሉም። ታዲያ ኢየሱስ የተናገረው ሐሳብ ምን ትርጉም አለው?

      ኤል ኤቫንሄልዮ ደ ማርኮስ፣ አናሊሲስ ሊንግዊስቲኮ ኢ ኮሜንታርዮ ኤክሴሄቲኮ በተባለው የካቶሊክ ጽሑፍ ጥራዝ ሁለት ላይ ስለ ማርቆስ 9:48 የተሰጠውን ሐሳብ እንመልከት:- “ይህ ሐረግ የተወሰደው ከኢሳይያስ (66,24) ነው። እዚህ ላይ ነቢዩ የገለጸው ብዙውን ጊዜ አስከሬን የሚወገድባቸውን ሁለት መንገዶች ይኸውም መበስበስንና መቃጠልን ነበር፤ . . . ትልና እሳት አንድ ላይ መጠቀሳቸው መጥፋት የሚለውን ሐሳብ ለማጠናከር ይረዳል። . . . ሁለቱም የጥፋት ኃይሎች ቀጣይ እንደሆኑ ተደርገው ተገልጸዋል (‘አይጠፋም፣ አይሞትም’)፤ ከእነዚህ ነገሮች በምንም መንገድ ማምለጥ አይቻልም። በዚህ ማብራሪያ ላይ እንደማይጠፉ ተደርገው የተጠቀሱት ሰዎቹ ሳይሆኑ ትሎቹና እሳቱ ብቻ ናቸው፤ እነዚህ ደግሞ ያገኙትን ሁሉ ድምጥማጡን ያጠፉታል። በመሆኑም ይህ ጥቅስ ዘላለማዊ ሥቃይን የሚያብራራ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ መጥፋትን የሚያመለክት ነው፤ ይህ ዓይነቱ ጥፋት ትንሣኤ የሌለው በመሆኑ ዘላለማዊ ነው። ስለዚህ [እሳት] ሙሉ በሙሉ የመጥፋት ምሳሌ ነው።”

  • ኢየሱስ የተናገረው ስለ ገሃነመ እሳት ነበር?
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | ሰኔ 15
    • b “ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትም፤ እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።”—ኢሳ. 66:24

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ