የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አዲሱ ዓለም—አንተም በዚያ ትገኝ ይሆን?
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | ሚያዝያ 15
    • 6. ስለ “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር” የሚጠቅሰው አራተኛው ትንቢት የሚተነብየው ምንድን ነው?

      6 አሁን በ⁠ኢሳይያስ 66:​22-24 ላይ የሚገኘውን “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር” የሚለው ሐረግ የተጠቀሰበትን አራተኛውን ቦታ እንመርምር። “እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፣ ይላል እግዚአብሔር። እንዲህ ይሆናል፤ በየመባቻውና በየሰንበቱ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በፊቴ ይሰግድ ዘንድ ዘወትር ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር። ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፣ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።”

      7. ኢሳይያስ 66:​22-24 በመጪዎቹ ጊዜያት ፍጻሜውን ያገኛል ብለን የምንደመድመው ለምንድን ነው?

      7 ይህ ትንቢት ወደ ትውልድ አገራቸው በተመለሱት አይሁዳውያን ላይ ይሠራ የነበረ ቢሆንም ሌላም ፍጻሜ ያለው ነው። የጴጥሮስ ሁለተኛ መልእክትና የራእይ መጽሐፍ ወደ ፊት ስለሚመጣ ‘አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር’ የሚናገሩ በመሆናቸው ይህ የሚከናወነው እነዚህ መጻሕፍት ከተጻፉበት ዘመን ብዙ ቆይቶ መሆን ይኖርበታል። በአዲሱ ሥርዓት ታላቅና የተሟላ ፍጻሜውን ያገኛል ብለን ልንጠብቅ እንችላለን። ወደፊት ይፈጸማሉ ብለን ልንጠብቃቸው ከምንችላቸው ሁኔታዎች መካከል አንዳንዶቹን እንመርምር።

  • አዲሱ ዓለም—አንተም በዚያ ትገኝ ይሆን?
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | ሚያዝያ 15
    • 10. ክፉ ሰዎች አዲሱን ዓለም እንደማያውኩት እርግጠኛ መሆን የምትችለው ለምንድን ነው?

      10 ኢሳይያስ 66:​24 በአዲሱ ምድር የሚሰፍነው ሰላምና ጽድቅ ፈጽሞ እንደማይደፈርስ ያረጋግጥልናል። ክፉ ሰዎች ፈጽመው አያበላሹትም። 2 ጴጥሮስ 3:​7 ከፊ​ታችን ‘አምላካዊ አክብሮት የሌላቸው ሰዎች የሚጠፉበት የፍርድ ቀን’ እንደሚጠብቀን የሚናገር መሆኑን አስታውስ። በሚመጣው የጥፋት ቀን የሚወገዱት አምላካዊ አክብሮት የሌላቸው ናቸው። ከወታደሮች ይልቅ ብዙ ሲቪሎች በሚገ​ደሉባቸው ሰብዓዊ ጦርነቶች ላይ እንደሚደርሰው ንጹሐን በሆኑ ሰዎች ላይ የሚደርስ ጉዳት አይኖርም። ከዚህ ይልቅ ታላቁ ፈራጅ በእርሱ ቀን የሚጠፉት አምላካዊ አክብሮት የሌላቸው እንደሚሆኑ ዋስትና ይሰጠናል።

      11. ኢሳይያስ ለአምላክና ለአምልኮው ጀርባቸውን የሚሰጡ ሰዎች የወደፊት እጣቸው ምን እንደሚሆን አመልክቷል?

      11 ከጥፋቱ በሕይወት የሚያልፉት ጻድቃን የአምላክ ትንቢታዊ ቃል እውነት መሆኑን ያመለክታሉ። ቁጥር 24 ‘በይሖዋ ላይ ያመፁ ሰዎች ሬሳ ለፍርዱ በማስረጃነት እንደሚታይ ይተነብያል። ኢሳይያስ የተጠቀመበት ሥዕላዊ መግለጫ የሚዘገንን ይመስል ይሆናል። ሆኖም ይህ ከአንድ ታሪካዊ ሐቅ ጋር የሚስማማ ነው። ከኢየሩሳሌም ቅጥር ውጭ ቆሻሻና አንዳንድ ጊዜም ክብር ያለው ቀብር ሊያገኙ የማይገባቸው ወንጀለኞች ሬሳ የሚጣልበት የቆሻሻ መጣያ ቦታ ነበር።a በዚያ የሚጣለው ቆሻሻም ሆነ የወንጀለኞቹ አስከሬን ብዙ ሳይቆይ በእሳትና በትል ተበልቶ ያልቃል። ኢሳይያስ ሕግ በሚተላለፉ ላይ የሚመጣው የይሖዋ ፍርድ የማያዳግምና የመጨረሻ መሆኑን ለመግለጽ ሲል ይህን ሁኔታ በምሳሌነት ተጠቅሟል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ