-
‘ይቅር ለማለት ዝግጁ’ የሆነ አምላክወደ ይሖዋ ቅረብ
-
-
“ኃጢአታችሁ . . . እንደ በረዶ ይነጣል”
10. ይሖዋ ኃጢአታችንን ይቅር ካለን በቀሪው የሕይወት ዘመናችን ኃጢአታችን ያስከተለብንን ኀፍረት ተሸክመን እንደምንኖር ሆኖ ሊሰማን የማይገባው ለምንድን ነው?
10 የመነቸከ ነጭ ልብስ ለማስለቀቅ ሞክረህ ታውቃለህ? የቱንም ያህል ብትፈትገው ቆሻሻው አልለቅ ይል ይሆናል። ይሁን እንጂ ይሖዋ ይቅር ባይነቱን እንዴት እንደገለጸው ልብ በል፦ “ኃጢአታችሁ እንደ ደም ቢቀላ እንደ በረዶ ይነጣል፤ እንደ ደማቅ ቀይ ጨርቅ ቢቀላም እንደ ነጭ የሱፍ ጨርቅ ይሆናል።”a (ኢሳይያስ 1:18) በራሳችን ጥረት ኃጢአታችንን ልናጠራ ወይም ልናስወግድ አንችልም። ይሁን እንጂ ይሖዋ እንደ ደም የቀላውን ወይም እንደ ደማቅ ቀይ የሆነውን ኃጢአታችንን እንደ በረዶ ወይም እንደ ነጭ የሱፍ ጨርቅ ነጭ ሊያደርገው ይችላል። ስለሆነም ይሖዋ ኃጢአታችንን አንዴ ይቅር ካለን በቀሪው የሕይወት ዘመናችን ሁሉ ኃጢአታችን ያስከተለብንን ኀፍረት ተሸክመን እንደምንኖር ሆኖ ሊሰማን አይገባም።
-
-
‘ይቅር ለማለት ዝግጁ’ የሆነ አምላክወደ ይሖዋ ቅረብ
-
-
a አንድ ምሁር እንደገለጹት እዚህ ላይ “እንደ ደም” ተብሎ የተተረጎመው የቀለም ዓይነት “የማይለቅ ወይም የማይደበዝዝ ነው። እርጥበት፣ ዝናብ፣ እጥበት ወይም የረጅም ጊዜ አገልግሎት ሊያስለቅቀው አይችልም።”
-