-
የሞቱ ሰዎች በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
2. ስለ ሞት እውነቱን ማወቃችን ምን ጥቅም ያስገኝልናል?
ብዙ ሰዎች ሞትን አልፎ ተርፎም የሞቱ ሰዎችን ይፈራሉ! መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሞት የሚናገረውን ነገር ማወቅ ግን ያጽናናል። ኢየሱስ ‘እውነት ነፃ ያወጣችኋል’ ብሏል። (ዮሐንስ 8:32) አንዳንድ ሃይማኖቶች ሰው ከሞተ በኋላ በሕይወት መኖሯን የምትቀጥል የማትሞት ነፍስ እንዳለች ያስተምራሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ አይልም። ማንም ሰው ከሞተ በኋላ አይሠቃይም። በተጨማሪም ሙታን ምንም ነገር ስለማያውቁ እኛን ሊጎዱን አይችሉም። እንዲሁም ከሞቱ ሰዎች ጋር በተያያዘ ለየት ያለ ሃይማኖታዊ ሥርዓት መፈጸም ወይም ስለ እነሱ መጸለይ አያስፈልገንም።
አንዳንዶች ‘የሞቱ ሰዎችን ማነጋገር እንችላለን’ ይላሉ። ሆኖም ይህ ሊሆን የማይችል ነገር ነው። ቀደም ሲል እንደተመለከትነው ‘ሙታን ምንም አያውቁም።’ በሞት የተለዩአቸውን ሰዎች እንደሚያነጋግሩ የሚያስቡ ሰዎች የሚያነጋግሩት የሞቱትን ሰዎች ሳይሆን እነሱን መስለው የሚቀርቡ አጋንንትን ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ሞትን በተመለከተ እውነቱን ማወቃችን ከአጋንንት ይጠብቀናል። ይሖዋ ከሞቱ ሰዎች ጋር ለመነጋገር መሞከር እንደሌለብን አስጠንቅቆናል፤ ምክንያቱም አጋንንት በዚህ ተጠቅመው ሊጎዱን እንደሚችሉ ያውቃል።—ዘዳግም 18:10-12ን አንብብ።
-
-
የሞቱ ሰዎች በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
4. ስለ ሞት እውነቱን ማወቃችን ይጠቅመናል
ሞትን በተመለከተ እውነቱን ማወቃችን የሞቱ ሰዎችን እንዳንፈራ ይረዳናል። መክብብ 9:10ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
የሞቱ ሰዎች ሊጎዱን ይችላሉ?
የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ማወቃችን ‘የሞቱ ሰዎች በሕይወት ያሉትን ሊጎዱ ይችላሉ’ ወይም ‘ሊመለኩ ይገባል’ ከሚለው እምነትም ይጠብቀናል። ኢሳይያስ 8:19ን እና ራእይ 4:11ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ለሞቱ ሰዎች አምልኮ የሚያቀርብን ወይም የእነሱን እርዳታ ለማግኘት የሚሞክርን ሰው በተመለከተ ይሖዋ ምን የሚሰማው ይመስልሃል?
ስለ ሞት እውነቱን ማወቃችን ይሖዋን ከሚያሳዝኑ ልማዶች እንድንርቅ ይረዳናል
-