-
የሰላም መስፍን እንደሚነሳ የተሰጠ ተስፋየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
15, 16. (ሀ) ‘የዛብሎንና የንፍታሌም’ አካባቢዎች ሁኔታ የሚለወጥበት ‘የኋለኛው ዘመን’ የትኛው ነው? (ለ) ያቃለሉት ምድር ክብር የሚላበሰው እንዴት ነው?
15 ሐዋርያው ማቴዎስ ስለ ኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎት በመንፈስ አነሳሽነት በጻፈው ዘገባ ውስጥ ለዚህ ጥያቄ መልሱን ይሰጣል። ማቴዎስ በዚህ የኢየሱስ አገልግሎት መጀመሪያ አካባቢ ስለነበሩት ሁኔታዎች ሲገልጽ እንዲህ ብሏል:- “[ኢየሱስ] ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ። በነቢዩም በኢሳይያስ:- የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር፣ የባሕር መንገድ፣ በዮርዳኖስ ማዶ፣ የአሕዛብ ገሊላ፤ በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፣ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።”—ማቴዎስ 4:13-16
-
-
የሰላም መስፍን እንደሚነሳ የተሰጠ ተስፋየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
“ታላቅ ብርሃን”
17. በገሊላ “ታላቅ ብርሃን” የወጣው እንዴት ነው?
17 ማቴዎስ በገሊላ እንደሚወጣ ስለተናገረለት ‘ታላቅ ብርሃንስ’ ምን ማለት ይቻላል? ይህም ቢሆን ከኢሳይያስ መጽሐፍ የተወሰደ ሐሳብ ነው። ኢሳይያስ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “በጨለማ የሄደ ሕዝብ [“ታላቅ፣” NW ] ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው።” (ኢሳይያስ 9:2) በመጀመሪያው መቶ ዘመን እዘአ የእውነት ብርሃን በአረማዊ የሐሰት ትምህርቶች ተቀብሮ ነበር። የአይሁድ ሃይማኖታዊ መሪዎች ደግሞ ‘የእግዚአብሔርን ቃል ሽረው’ ሃይማኖታዊ ወጋቸውን የሙጥኝ በማለት ችግሩን አባብሰውት ነበር። (ማቴዎስ 15:6) ከታች ያሉት ሰዎች ‘እውር የሆኑ መሪዎችን’ እየተከተሉ ለጭቆናና ግራ መጋባት ተዳርገው ነበር። (ማቴዎስ 23:2-4, 16) መሲሑ ኢየሱስ በተገለጠ ጊዜ ከሥር የነበሩት የብዙዎቹ ሰዎች ዓይን አስገራሚ በሆነ መንገድ ተከፈተ። (ዮሐንስ 1:9, 12) ኢየሱስ በምድር ላይ ያከናወነው ሥራና በመሥዋዕቱ አማካኝነት የተገኙት በረከቶች በኢሳይያስ መጽሐፍ ውስጥ እንደ “ታላቅ ብርሃን” ተደርገው መገለጻቸው ትክክል ነው።—ዮሐንስ 8:12
-
-
የሰላም መስፍን እንደሚነሳ የተሰጠ ተስፋየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
[በገጽ 127 ላይ የሚገኝ የሥዕል መግለጫ]
ኢየሱስ ለምድሪቱ ብርሃን ሆኖ ነበር
-