የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ለዓመፀኞች ወዮላቸው!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 1. ኢዮርብዓም የፈጸመው ከባድ ስህተት ምን ነበር?

      የይሖዋ የቃል ኪዳን ሕዝብ ለሁለት መንግሥት በተከፈለ ጊዜ ሰሜናዊውን የአሥሩን ነገድ መንግሥት ኢዮርብዓም ተቆጣጠረው። አዲሱ ንጉሥ ብቃት ያለው ብርቱ ገዢ ነበር። ይሁን እንጂ በይሖዋ ላይ ጠንካራ እምነት አልነበረውም። ከዚህ የተነሣ የሰሜናዊውን መንግሥት ታሪክ በእጅጉ ያመሰቃቀለ ከባድ ስህተት ሠርቷል። እስራኤላውያን በዓመት ሦስት ጊዜ ያህል ወደ ቤተ መቅደሱ እንዲሄዱ የሙሴ ሕግ ያዝዝ ነበር። በዚህ ጊዜ ደግሞ ቤተ መቅደሱ የነበረው በደቡባዊው የይሁዳ ግዛት ውስጥ ነው። (ዘዳግም 16:​16) ኢዮርብዓም ተገዢዎቹ ዘወትር እንዲህ ያለውን ጉዞ የሚያደርጉ ከሆነ ከደቡባዊ ወንድሞቻችን ጋር እንቀላቀል የሚል ሐሳብ ይመጣባቸዋል ብሎ ስለፈራ “ሁለትም የወርቅ ጥጃዎች አድርጎ:- እስራኤል ሆይ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ትወጡ ዘንድ ይበዛባችኋል፤ ከግብጽ ምድር ያወጡህን አማልክቶችህን እይ አላቸው። አንዱን በቤቴል፣ ሁለተኛውንም በዳን አኖረ።”​—⁠1 ነገሥት 12:​28, 29

      2, 3. ኢዮርብዓም የሠራው ስህተት በእስራኤል ላይ ያስከተለው ውጤት ምንድን ነው?

      2 ለጊዜው የኢዮርብዓም ዕቅድ የሰመረለት ይመስል ነበር። ሕዝቡ ቀስ በቀስ ወደ ኢየሩሳሌም መሄዱን ተወና ለሁለቱ ጥጃዎች ይሰግድ ጀመር። (1 ነገሥት 12:​30) ይሁን እንጂ ይህ ሃይማኖታዊ የክህደት ተግባር የአሥሩን ነገድ መንግሥት አበላሽቶታል። በኋለኛው ዘመን የተነሣውና የበኣልን አምልኮ ከእስራኤል ጠራርጎ በማስወገድ ረገድ እጅግ ከፍተኛ ቅንዓት ያሳየው ኢዩ እንኳ ሳይቀር ለወርቅ ጥጃዎቹ መስገዱን ቀጥሏል። (2 ነገሥት 10:​28, 29) አሳዛኝ የሆነው የኢዮርብዓም የተሳሳተ ውሳኔ ያስከተለው ሌላው ውጤት ምን ነበር? ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ነግሦና ሕዝቡም ለሰቆቃ ተዳርጎ ነበር።

      3 ኢዮርብዓም ከሃዲ ሆኖ ስለነበር ዘሩ ምድሪቱን እንደማይገዛና በመጨረሻም ሰሜናዊው መንግሥት ከባድ ችግር ላይ እንደሚወድቅ ይሖዋ ተናግሮ ነበር። (1 ነገሥት 14:​14, 15) ደግሞም የተናገረው ቃል በትክክል ተፈጽሟል። ከእስራኤል ነገሥታት መካከል ሰባቱ ሥልጣን ላይ የቆዩት ለሁለት ዓመትና ከዚያም ላነሰ ጊዜ ሲሆን አንዳንዶቹም የገዙት ለጥቂት ቀናት ብቻ ነበር። አንድ ንጉሥ የገዛ ሕይወቱን ሲያጠፋ ስድስት ነገሥታት ደግሞ ዙፋናቸውን በገለበጡት የሥልጣን ጥመኛ ሰዎች ተገድለዋል። በተለይ በ804 ከዘአበ ካበቃው ከዳግማዊ ኢዮርብዓም ግዛት በኋላ ንጉሥ ዖዝያን በይሁዳ እየገዛ ሳለ እስራኤል አለመረጋጋት፣ ዓመፅና ግድያ ሞልቶባት ነበር። ይሖዋ በኢሳይያስ በኩል ለሰሜናዊው መንግሥት ቀጥተኛ ማስጠንቀቂያ ወይም “ቃል” የላከው ይህን ሁኔታ በመቃወም ነው። “ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃልን ሰደደ፣ በእስራኤልም ላይ ወደቀ።”​—⁠ኢሳይያስ 9:​8a

  • ለዓመፀኞች ወዮላቸው!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • a ኢሳይያስ 9:​8–10:​4 ላይ ያሉት አራት የግጥም አንቀጾች ሲሆኑ እያንዳንዳቸው የሚደመደሙት “በዚህም ሁሉ እንኳ ቁጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች” በሚለው የማስጠንቀቂያ አዝማች ነው። (ኢሳይያስ 9:​12, 17, 21፤ 10:​4) ይህ የአጻጻፍ ዘይቤ ኢሳይያስ 9:​8–10:​4ን እንደ አንድ “ቃል” አስተሳስሯቸዋል። (ኢሳይያስ 9:​8) የይሖዋ እጅ ‘ገና ተዘርግታ ያለችው’ ለእርቅ ሳይሆን ፍርድ ለመስጠት እንደሆነ ልብ በል።​—⁠ኢሳይያስ 9:​13

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ