የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ለዓመፀኞች ወዮላቸው!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • የሐሰት አምልኮ ዓመፅን ያስፋፋል

      14, 15. (ሀ) የአጋንንት አምልኮ የሚያስከትለው ውጤት ምንድን ነው? (ለ) ኢሳይያስ የተነበየው እስራኤል ምን ቀጣይ የሆነ መከራ እንደሚደርስባት ነው?

      14 የሐሰት አምልኮ ማለት የአጋንንት አምልኮ ማለት ነው። (1 ቆሮንቶስ 10:​20) ከጥፋት ውኃ በፊት እንደታየው ደግሞ የአጋንንት ተጽእኖ ወደ ዓመፅ ይመራል። (ዘፍጥረት 6:​11, 12) እንግዲያው እስራኤላውያን ከሃዲዎች ሲሆኑና በአጋንንት አምልኮ ውስጥ መግባት ሲጀምሩ ምድሪቱ በዓመፅና በክፋት መታመሷ ምንም አያስገርምም።​—⁠ዘዳግም 32:​17፤ መዝሙር 106:​35-38

      15 ኢሳይያስ በእስራኤል ውስጥ ክፋትና ዓመፅ መስፋፋቱን እንደሚከተለው በማለት በግልጽ አስቀምጦታል:- “ክፋት እንደ እሳት ይቃጠላል፤ ኩርንችቱንና እሾሁን ይበላል፤ ጭፍቅ የሆነውንም ዱር ያቃጥላል፣ ጢሱም ተትጐልጉሎ እንደ ዓምድ ይወጣል። በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቁጣ ምድር ተቃጥላለች፤ ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፤ ሰውም ለወንድሙ አይራራም። ሰው በቀኙ በኩል ይነቅላል ይራብማል፤ በግራም በኩል ይበላል አይጠግብምም፤ እያንዳንዱም የክንዱን ሥጋ ይበላል፤ ምናሴ ኤፍሬምን ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፤ እነርሱ በአንድነት የይሁዳ ጠላቶች ይሆናሉ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቁጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።”​—⁠ኢሳይያስ 9:​18-21

      16. የ⁠ኢሳይያስ 9:​18-21 ቃላት ፍጻሜያቸውን ያገኙት እንዴት ነው?

      16 ከኩርንችት ወደ ኩርንችት እንደሚዛመት እሳት ዓመፁ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በፍጥነት ‘ጭፍቅ ወደሆነው ዱር’ ይደርስና ሙሉ በሙሉ እንደተያያዘ የደን እሳት ይሆናል። የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኝ የሆኑት ካርል እና ዴሊትሽ በወቅቱ የነበረው ዓመፅ ምን ያህል እንደነበር ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል:- “ድብልቅልቅ ባለ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት የታየ የከፋ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ነው። ርኅራኄ በሌለው መንገድ እርስ በርሳቸው ቢጨራረሱም የልባቸው አልደረሰም።” የኤፍሬምና የምናሴ ነገድ እዚህ ላይ ተለይተው የተጠቀሱት የሰሜናዊው መንግሥት ዋነኛ ወኪሎች በመሆናቸው እንዲሁም የሁለቱ የዮሴፍ ልጆች ዝርያ እንደመሆናቸው መጠን ከአሥሩ ነገዶች መካከል የበለጠ ቅርርብ ስለነበራቸው ይመስላል። እንደዚያም ሆኖ ግን እርስ በርስ መበላላታቸውን የሚያቆሙት በደቡብ ከምትገኘው ይሁዳ ጋር ሲዋጉ ብቻ ነው።​—⁠2 ዜና መዋዕል 28:​1-8

  • ለዓመፀኞች ወዮላቸው!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • [በገጽ 139 ላይ የሚገኝ ባለ ሙሉ ገጽ ሥዕል]

      ክፋትና ዓመፅ እስራኤልን እንደ ጫካ እሳት አዳርሷታል

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ