የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ለዓመፀኞች ወዮላቸው!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 17, 18. በእስራኤል የሕግና የአስተዳደር መዋቅር ውስጥ ምን ብልሹነት ይታያል?

      17 ቀጥሎ ይሖዋ ፍርድ ለመስጠት ዓይኑን የሚያሳርፈው ብልሹ በሆኑት የእስራኤል መሳፍንትና ሌሎች ባለ ሥልጣናት ላይ ነው። እነዚህ ሰዎች ፍትሕ ፍለጋ ወደ እነርሱ የሚመጡትን ድሆችና ችግረኞች በመበዝበዝ ሥልጣናቸውን አላግባብ ይጠቀማሉ። ኢሳይያስ እንዲህ ይላል:- “መበለቶችም ቅሚያቸው እንዲሆኑ፣ ድሀ አደጎችንም [“አባት የሌላቸውንም ልጆች፣” NW] ብዝበዛቸው እንዲያደርጉ፣ የድሀውን ፍርድ ያጣምሙ ዘንድ፣ የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ ያጐድሉ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ፣ ክፉንም ጽሕፈት ለሚጽፉ ወዮላቸው!”​—⁠ኢሳይያስ 10:​1, 2

      18 የይሖዋ ሕግ ማንኛውንም ዓይነት የፍትሕ መጓደል ያወግዛል:- “በፍርድ ዓመፃ አታድርጉ፤ ለድሀ አታድላ፣ ባለ ጠጋውንም አታክብር።” (ዘሌዋውያን 19:​15) እነዚህ ባለ ሥልጣናት ይህንን ሕግ ወደ ጎን በመተው የመበለቶችንና አባት የሌላቸውን ልጆች የመጨረሻ ጥሪት በማሟጠጥ የከፋ ጭካኔ የሚንጸባረቅበት ዓይን ያወጣ ሌብነት ለመፈጸም ሲሉ የራሳቸውን ‘የግፍ ትእዛዝ’ ጽፈዋል። እርግጥ ነው የእስራኤል የሐሰት አማልክት ይህን የፍትሕ መጓደል የሚያስተውሉበት ዓይን የላቸውም። ይሖዋ ግን ችላ ብሎ አያልፈውም። ይሖዋ አሁን በኢሳይያስ አማካኝነት ትኩረቱን ያደረገው በእነዚህ ክፉ መሳፍንት ላይ ነው።

  • ለዓመፀኞች ወዮላቸው!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • [በገጽ 141 ላይ የሚገኝ ባለ ሙሉ ገጽ ሥዕል]

      ሌሎችን የሚበዘብዙትን ሰዎች ይሖዋ ወደ ፍርድ ያመጣቸዋል

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ