-
በመሲሑ ግዛት የሚገኝ መዳንና ደስታየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
4, 5. ኢሳይያስ የመሲሑን መምጣት በተመለከተ ምን ትንቢት ተናግሯል? ማቴዎስ ጠቅሶ የተናገረው የትኞቹን የኢሳይያስ ቃላት ነው?
4 ከኢሳይያስ ዘመን ብዙ መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ ሌሎች ዕብራውያን የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎችም ስለ መሲሑ ማለትም ይሖዋ ወደ እስራኤል ስለሚልከው እውነተኛ መሪ መምጣት ተናግረው ነበር። (ዘፍጥረት 49:10፤ ዘዳግም 18:18፤ መዝሙር 118:22, 26) አሁን ደግሞ ይሖዋ በኢሳይያስ አማካኝነት ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን ይገልጻል። ኢሳይያስ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፣ ከሥሩም ቁጥቋጥ ያፈራል። ” (ኢሳይያስ 11:1፤ ከመዝሙር 132:11 ጋር አወዳድር።) “በትር” እና “ቁጥቋጥ” የሚሉት ሁለቱም መግለጫዎች መሲሑ የእስራኤል ንጉሥ ሆኖ በዘይት በተቀባው በእሴይ ልጅ በዳዊት በኩል የሚመጣ የእሴይ ዘር እንደሆነ የሚያመለክቱ ናቸው። (1 ሳሙኤል 16:13፤ ኤርምያስ 23:5፤ ራእይ 22:16) እውነተኛው መሲሕ ማለትም ከዳዊት ቤት የሚወጣው ይህ “ቁጥቋጥ” ሲመጣ መልካም ፍሬዎችን ያፈራል።
5 ተስፋ የተሰጠበት መሲሕ ኢየሱስ ነው። የወንጌል ጸሐፊ የሆነው ማቴዎስ ኢየሱስ “ናዝራዊ” ተብሎ መጠራቱ የነቢያት ቃል ፍጻሜ ነው ብሎ ሲጽፍ በተዘዋዋሪ መንገድ ኢሳይያስ 11:1ን መጥቀሱ ነበር። ኢየሱስ ያደገው በናዝሬት ከተማ በመሆኑ ናዝራዊ ተብሎ ተጠርቷል። ይህ ስም በኢሳይያስ 11:1 ላይ ከተጠቀሰው “ቁጥቋጥ” የሚል ትርጉም ካለው የዕብራይስጥ ቃል ጋር የሚዛመድ ነው።b—ማቴዎስ 2:23፣ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ፤ ሉቃስ 2:39, 40
-
-
በመሲሑ ግዛት የሚገኝ መዳንና ደስታየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
b “ቁጥቋጥ” የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ኔሰር ሲሆን “ናዝራዊ” የሚለው ደግሞ ኖስሪ ነው
-