የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የዔድን ገነት በመላው ምድር ላይ እንደገና ትቋቋማለች
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
    • 6, 7. (ሀ) የእንስሳት ፍጥረት ለሰዎች አስጊ የማይሆነው ለምንድን ነው? (ለ) ይህንን በሚመለከት የትኛው ትንቢት ቃል በቃል ይፈጸማል?

      6 እንደገና በምትቋቋመዋ ገነት ውስጥ የእንስሳት ፍጥረት ጉዳት አያደርሱም፤ ለነዋሪዎቹም አስጊ አይሆኑም። በዝቅተኛ ፍጥረቶች ላይ በመጠኑ ጠፍቶ የነበረውን ሰዎችን የመፍራት ባሕርይ አምላክ ይመልሳል። በዚህም ምክንያት ‘በሰላሙ መስፍን’ የሺህ ዓመት ግዛት ውስጥ ስለሚኖረው የእንስሳት ሕይወት በኢሳይያስ 11:6–9 ላይ የተገለጸው አስደሳች መግለጫ ቃል በቃል እንደሚፈጸም ለመጠበቅ እንችላለን:-

      7 “ተኩላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል፣ ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል፤ ጥጃና የአንበሳ ደቦል ፍሪዳም በአንድነት ያርፋሉ፤ ታናሽም ልጅ ይመራቸዋል። ላምና ድብ አብረው ይሰማራሉ፣ ግልገሎቻቸውም በአንድነት ያርፋሉ፤ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል። የሚጠባውም ሕፃን በእባብ ጉድጓድ ላይ ይጫወታል፣ ጡት የጣለውም ሕፃን በእፉኝት ቤት ላይ እጁን ይጭናል። በተቀደሰውም ተራራዬ ሁሉ ላይ አይጎዱም አያጠፉምም፤ ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር [ይሖዋን (አዓት)] በማወቅ ትሞላለችና።”

      8. የእባብ መብል “ትቢያ ይሆናል” የሚለው ትንቢታዊ አነጋገር ትርጉም ምንድን ነው?

      8 እንደዚህ ያለውን ትንቢት መንፈሳዊ ትርጉም ብቻ ቢኖረውና እንደዚህ ያሉት ነገሮች በምድራዊ ሕይወት ውስጥ ቃል በቃል እንዳይንፀባረቁ ቢያደርግ የአምላክን አቋም ተለዋዋጭ ያደርገዋል። በተመሳሳይም ኢሳይያስ 65:25 “ተኩላና ጠቦት በአንድነት ይሰማራሉ፣ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፣ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል” በማለት ይነግረናል። ይህ ሲባል የእባብ ዘር ከምድር አቀፍዋ የዔድን ገነት ይጠፋል ማለት ነውን? አይደለም። የእባብ መብል “ትቢያ ይሆናል” ሲባል በሆዳቸው የሚሳቡ ፍጥረታት ዝርያዎች እንደገና ለሰብዓዊ ፍጥረታት ሕይወትና መልካም ጤንነት ፈጽሞ አስጊ አይሆኑም ማለት ነው። ልክ አዳም ለሁሉም እንስሳት ያለ ፍርሃት ስም ባወጣበት ጊዜ እንደነበረው የሰው ዘር በምድር ላይ በሚንቀሳቀሰው ነገር ሁሉ ላይ የሚገዛ ጌታቸው መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።— ዘፍጥረት 2:19, 20፤ ሆሴዕ 2:18 አዓት። (በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ሆሴዕ 2:20)

  • የዔድን ገነት በመላው ምድር ላይ እንደገና ትቋቋማለች
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
    • 11. በቋንቋ ምን ለውጥ ይደረጋል? ይህስ የሰውን ዘር እንዴት ይነካል?

      11 ምድር አቀፍዋ ገነት ብዙ ቋንቋ በመኖሩ ምክንያት በሚመጣ ዝብርቅ ችግር ያጋጥማት ይሆንን? አይሆንም፤ ምክንያቱም ‘የሰላሙ መስፍን’ “ኃያል አምላክ” ተብሎም ተጠርቷል። (ኢሳይያስ 9:6) ስለዚህ የባቤል ግንብ በሚሠራበት ጊዜ የጀመረውን የቋንቋ ዝብርቅ ሊያስተካክለው ይችላል። (ዘፍጥረት 11:6–9) ‘የዘላለሙ አባት’ ምድራዊ ልጆች በሙሉ የጋራ ቋንቋቸው የሚሆነው ምንድን ነው? የፊተኛው አዳም የመጀመሪያ ቋንቋ ማለትም ይሖዋ የሰጠው ቋንቋ ይሆንን? ሳይሆን አይቀርም። በዚህም ይሁን በዚያ ሁሉም የቋንቋ አጥሮች ይወገዳሉ። የትም ቦታ ለመጓዝና ከሰዎች ጋር ሐሳብ ለሐሳብ መለዋወጥ ትችላለህ። እነርሱ የሚናገሩትን ለመረዳት ትችላለህ፤ እነርሱም አንተ የምትናገረውን ሊረዱ ይችላሉ። ለሁሉም የሰው ዘር አንድ ቋንቋ ይሆናል፣ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስም በዚሁ ቋንቋ መዘጋጀቱ ተገቢ ይሆናል። (ከሶፎንያስ 3:9 ጋር አወዳድር) “ውኃ ባሕርን እንደሚከድን” በዚህ ቋንቋ ምድር ሁሉ በይሖዋ እውቀት ትሞላለች።— ኢሳይያስ 11:9

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ