የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አባትና ዓመፀኛ ልጆቹ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • ማስተዋል የሌላቸው እንስሳት ተሻሉ

      5. ከእስራኤላውያን በተቃራኒ በሬና አህያ በተወሰነ መጠን ታማኝ መሆናቸውን የሚያሳዩት በምን መንገድ ነው?

      5 ይሖዋ በኢሳይያስ በኩል እንዲህ አለ:- “በሬ የገዢውን አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ፤ እስራኤል ግን አላወቀም፣ ሕዝቤም አላስተዋለም።” (ኢሳይያስ 1:3)a በሬና አህያ ጭነት ለመጎተት የሚያገለግሉ በመካከለኛው ምሥራቅ በሚኖሩ ሰዎች ዘንድ የተለመዱ እንስሳት ናቸው። በእርግጥም ደግሞ እነዚህ ተራ እንስሳት እንኳ በተወሰነ መጠን ታማኝነት የሚያሳዩና ጌታ እንዳላቸው የሚገነዘቡ መሆናቸው ከአይሁዳውያኑ የተሠወረ አልነበረም። በዚህ ረገድ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተመራማሪ በመካከለኛው ምሥራቅ በምትገኝ አንድ ከተማ አመሻሹ ላይ ምን ነገር እንዳስተዋሉ ልብ በል:- “ከብቶቹ ወደ ከተማዋ ቅጥር እንደገቡ ወዲያውኑ በየፊናቸው ያቀናሉ። እያንዳንዱ በሬ ባለቤቱንና ወደ ቤቱ የሚወስደውን መንገድ ጠንቅቆ ያውቃል። ጠባብና ጠመዝማዛ በሆኑት ግራ የሚያጋቡ መንገዶች ትንሽ እንኳ አይደናገርም። አህያውም ቢሆን ቀጥ ብሎ ወደ በሩ በመሄድ ‘ወደ ጌታው ጋጣ’ ያመራል።”

      6. የይሁዳ ሕዝብ ሳያስተውል የቀረው እንዴት ነው?

      6 በኢሳይያስ ዘመን እንዲህ ያሉትን ነገሮች ማየት የተለመደ በመሆኑ ይሖዋ ሊያስተላልፈው የፈለገው መልእክት ግልጽ ነበር:- አእምሮ የሌለው እንስሳ እንኳ ጌታውንና ጋጣውን ለይቶ ካወቀ የይሁዳ ሕዝብ ይሖዋን ስለተወበት ምክንያት ምን ሰበብ ሊያቀርብ ይችላል? በእርግጥም ‘አላስተዋሉም።’ ብልጽግናቸው ብሎም ሕልውናቸው የተመካው በይሖዋ ላይ መሆኑን በማስተዋል ረገድ አእምሮ አጥተው ነበር ለማለት ይቻላል። ይሖዋ በዚህ ጊዜም እንኳ የይሁዳን ሰዎች “ሕዝቤ” ብሎ መጥራቱ በእርግጥ ምህረቱን የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው!

      7. ለይሖዋ ዝግጅቶች አድናቆት እንዳለን ልናሳይ የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው?

      7 ይሖዋ ላደረገልን ነገር ሁሉ አድናቆት ሳናሳይ ቀርተን ማስተዋል የጎደለን ሆነን መገኘት አንፈልግም! ከዚህ ይልቅ “አቤቱ፣ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፣ ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ” ያለውን መዝሙራዊ ዳዊትን መምሰል ይኖርብናል። (መዝሙር 9:​1) መጽሐፍ ቅዱስ ‘ቅዱሱን ማወቅ ማስተዋል ነው’ በማለት ስለሚናገር ዘወትር ስለ ይሖዋ መማራችን ይህን ለማድረግ የሚያበረታታ ሆኖ እናገኘዋለን። (ምሳሌ 9:10) ከይሖዋ የምናገኛቸውን በረከቶች በተመለከተ በየዕለቱ ማሰላሰል አመስጋኞች እንድንሆንና ሰማያዊ አባታችንን ችላ እንዳንል ይረዳናል። (ቆላስይስ 3:​15) ይሖዋ እንዲህ ይላል:- “ምስጋናን የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።”​—⁠መዝሙር 50:​23

  • አባትና ዓመፀኛ ልጆቹ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • a እዚህ ጥቅስ ላይ “እስራኤል” የሚለው መጠሪያ የሚያመለክተው ሁለቱን ነገድ የይሁዳ መንግሥት ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ