የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ ኩሩዋን ከተማ ያዋርዳል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 17, 18. የባቢሎን ሽንፈት ለእስራኤል በረከት የሚሆነው እንዴት ነው?

      17 የባቢሎን መውደቅ ለእስራኤል እፎይታ ነው። ከምርኮ ነፃ ወጥተው ወደ ተስፋይቱ ምድር የመመለስ አጋጣሚ ይከፍትላቸዋል። በመሆኑም ኢሳይያስ እንዲህ ይላል:- “እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል፣ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፣ በአገራቸውም ያኖራቸዋል፤ መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፣ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃል። አሕዛብም ይዘው ወደ ስፍራቸው ያመጡአቸዋል፣ የእስራኤልም ቤት በእግዚአብሔር ምድር እንደ ሎሌዎችና እንደ ገረዶች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ የማረኩአቸውን ይማርካሉ፣ አስጨናቂዎችንም ይገዛሉ።” (ኢሳይያስ 14:​1, 2) እዚህ ላይ “ያዕቆብ” የሚለው መጠሪያ መላውን የእስራኤል 12 ነገድ የሚያመለክት ነው። ይሖዋ ብሔሩ ወደ ምድሩ እንዲመለስ በማድረግ ‘ለያዕቆብ’ ምሕረቱን ያሳያል። ከእነርሱ ጋር በሺህ የሚቆጠሩ መጻተኞች አብረው የሚሄዱ ሲሆን ብዙዎቹም እስራኤላውያንን በቤተ መቅደስ ያገለግላሉ። እንዲያውም አንዳንድ እስራኤላውያን በቀድሞ ማራኪዎቻቸው ላይ የሚገዙ ባለ ሥልጣናት ይሆናሉ።c

  • ይሖዋ ኩሩዋን ከተማ ያዋርዳል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 19. እስራኤል የይሖዋን ይቅርታ ለማግኘት ምን ማድረግ ያስፈልጋት ነበር? እኛስ ከዚህ ምን እንማራለን?

      19 ይሁን እንጂ የይሖዋን ምሕረት እንዲሁ ያገኛሉ ማለት አልነበረም። ከአምላክ ዘንድ ከባድ ቅጣት ላስከተለባቸው የክፋት ድርጊታቸው መጸጸታቸውን ሊያሳዩ ይገባ ነበር። (ኤርምያስ 3:​25) ምንም ሳያስቀሩ ከልብ መናዘዝ የይሖዋን ይቅርታ ያስገኝላቸዋል። (ነህምያ 9:​6-37⁠ንና ዳንኤል 9:​5ን ተመልከት።) ይኸው መሠረታዊ ሥርዓት ዛሬም ይሠራል። ‘የማይበድል ሰው ስለሌለ’ ሁላችንም የይሖዋ ምሕረት ያስፈልገናል። (2 ዜና መዋዕል 6:​36) መሐሪ የሆነው አምላክ ይሖዋ ፈውስ እናገኝ ዘንድ ኃጢአታችንን ለእርሱ እንድንናዘዝ፣ ንስሐ እንድንገባ እንዲሁም ክፉ ድርጊታችንን እንድንተው ፍቅራዊ ግብዣ ያቀርብልናል። (ዘዳግም 4:​31፤ ኢሳይያስ 1:​18፤ ያዕቆብ 5:​16) ይህ መልሰን ሞገሱን እንድናገኝ ብቻ ሳይሆን እንድንጽናናም ይረዳናል።​—⁠መዝሙር 51:​1፤ ምሳሌ 28:​13፤ 2 ቆሮንቶስ 2:​7

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ