የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ ኩሩዋን ከተማ ያዋርዳል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 17, 18. የባቢሎን ሽንፈት ለእስራኤል በረከት የሚሆነው እንዴት ነው?

      17 የባቢሎን መውደቅ ለእስራኤል እፎይታ ነው። ከምርኮ ነፃ ወጥተው ወደ ተስፋይቱ ምድር የመመለስ አጋጣሚ ይከፍትላቸዋል። በመሆኑም ኢሳይያስ እንዲህ ይላል:- “እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል፣ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፣ በአገራቸውም ያኖራቸዋል፤ መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፣ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃል። አሕዛብም ይዘው ወደ ስፍራቸው ያመጡአቸዋል፣ የእስራኤልም ቤት በእግዚአብሔር ምድር እንደ ሎሌዎችና እንደ ገረዶች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ የማረኩአቸውን ይማርካሉ፣ አስጨናቂዎችንም ይገዛሉ።” (ኢሳይያስ 14:​1, 2) እዚህ ላይ “ያዕቆብ” የሚለው መጠሪያ መላውን የእስራኤል 12 ነገድ የሚያመለክት ነው። ይሖዋ ብሔሩ ወደ ምድሩ እንዲመለስ በማድረግ ‘ለያዕቆብ’ ምሕረቱን ያሳያል። ከእነርሱ ጋር በሺህ የሚቆጠሩ መጻተኞች አብረው የሚሄዱ ሲሆን ብዙዎቹም እስራኤላውያንን በቤተ መቅደስ ያገለግላሉ። እንዲያውም አንዳንድ እስራኤላውያን በቀድሞ ማራኪዎቻቸው ላይ የሚገዙ ባለ ሥልጣናት ይሆናሉ።c

  • ይሖዋ ኩሩዋን ከተማ ያዋርዳል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • c ለምሳሌ ያህል ዳንኤል በሜዶንና ፋርስ መንግሥት ሥር የባቢሎን ከፍተኛ ባለ ሥልጣን ሆኖ ተሾሞ ነበር። ከ60 ዓመታት ገደማ በኋላ ደግሞ አስቴር የፋርሱ ንጉሥ የአሕሻዊሮስ ንግሥት ሆና የነበረ ሲሆን መርዶክዮስ በመላው የፋርስ ግዛት ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ሆኖ ተሾሞ ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ