-
ይሖዋ በብሔራት ላይ የመከረው ምክርየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
6 ይህ ለአዲሱ ንጉሥ ተስማሚ መግለጫ ነበር። ‘ፍልጥኤማውያንን እስከ ጋዛና እስከ ዳርቻዋ ድረስ የመታው ሕዝቅያስ’ ነው። (2 ነገሥት 18:8) የአሦር ንጉሥ የነበረው የሰናክሬም ዜና ታሪክ እንደሚለው ከሆነ ፍልስጥኤም የሕዝቅያስ ተገዥ ሆና ነበር። ፍልስጥኤም በረሃብ ስትሰቃይ ‘ድሀ ’ የተባለው የተዳከመው የይሁዳ መንግሥት አስተማማኝ ደህንነትና የተትረፈረፈ ቁሳዊ ነገር ያገኛል።—ኢሳይያስ 14:30, 31ን አንብብ።
-
-
ይሖዋ በብሔራት ላይ የመከረው ምክርየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
8. (ሀ) ዛሬ አንዳንድ ብሔራት እንደ ፍልስጥኤም የሆኑት እንዴት ነው? (ለ) ይሖዋ ጥንት እንዳደረገው ሁሉ ዛሬ ያሉትን ሕዝቦቹን ለመደገፍ ምን አድርጓል?
8 ዛሬም አምላክን የሚያመልኩ ሰዎችን ልክ እንደ ፍልስጥኤም አጥብቀው የሚቃወሙ አንዳንድ ብሔራት አሉ። ክርስቲያን የይሖዋ ምሥክሮች በእስር ቤቶችና በማጎሪያ ካምፖች ውስጥ ተጥለዋል። ሥራቸው ታግዷል። የተወሰኑትም ተገድለዋል። ተቃዋሚዎች ‘በጻድቅ ነፍስ ላይ ማድባታቸውን’ አይተዉም። (መዝሙር 94:21) ይህ የክርስቲያኖች ቡድን በጠላቶቹ ፊት እንደ ‘ድሃና’ ‘ችግረኛ’ ሆኖ ሊታይ ይችላል። ይሁን እንጂ በይሖዋ እርዳታ ጠላቶቻቸው በረሃብ ሲሰቃዩ እነርሱ በተትረፈረፈ መንፈሳዊ ነገር ደስ ይላቸዋል። (ኢሳይያስ 65:13, 14፤ አሞጽ 8:11) ይሖዋ በዘመናችን ፍልስጥኤማውያን ላይ እጁን ሲዘረጋ እነዚህ “ድሆች” መሸሸጊያ ያገኛሉ። የሚሸሸጉት የት ነው? ኢየሱስ የማዕዘን ድንጋይ ከሆነለት ‘የእግዚአብሔር ቤተሰብ’ ዘንድ ነው። (ኤፌሶን 2:19, 20) ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሥ የሆነለትን የይሖዋ ሰማያዊ መንግሥት ማለትም ‘የሰማያዊቱ ኢየሩሳሌምን’ ጥበቃም ያገኛሉ።—ዕብራውያን 12:22፤ ራእይ 14:1
-