የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ በብሔራት ላይ የመከረው ምክር
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 25. በ⁠ኢሳይያስ 19:​1-11 ፍጻሜ መሠረት የጥንቷ ግብጽ ምን ደርሶባታል?

      25 በስተ ደቡብ በኩል የምትገኘው የይሁዳ የቅርብ ጎረቤት ግብጽ ከረጅም ጊዜ አንስቶ የአምላክ የቃል ኪዳን ሕዝብ ጠላት ነበረች። ኢሳይያስ ምዕራፍ 19 በነቢዩ የሕይወት ዘመን ግብጽ ውስጥ የነበረውን ያልተረጋጋ ሁኔታ ይዘግባል። ግብጽ ውስጥ ‘ከተማ በከተማ ላይ መንግሥት በመንግሥት ላይ እየተነሳ’ የሚካሄድ የእርስ በርስ ጦርነት ነበር። (ኢሳይያስ 19:​2, 13, 14) ታሪክ ጸሐፊዎች በተመሳሳይ ወቅት የተለያዩ የአገሪቱን ክፍሎች የሚቆጣጠሩ ተቀናቃኝ ሥርወ መንግሥታት እንደነበሩ የሚያሳይ ማስረጃ ያቀርባሉ። እጅግ የሚኩራሩበት ጥበብም ሆነ ‘ከንቱ አማልክቶቻቸውና የሚጠነቁሉ መናፍስት ጠሪዎቻቸው’ ግብጽን ‘ከጨካኝ ጌታ እጅ’ ሊያድኗት አልቻሉም። (ኢሳይያስ 19:​3, 4) ግብጽ ተራ በተራ በአሦር፣ በባቢሎን፣ በፋርስ፣ በግሪክ እና በሮም ድል ተነስታለች። እነዚህ ሁሉ ክንውኖች በ⁠ኢሳይያስ 19:​1-11 ላይ ያለው ትንቢት ፍጻሜውን እንዳገኘ የሚያሳዩ ናቸው።

  • ይሖዋ በብሔራት ላይ የመከረው ምክር
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 28. በፍርድ ቀን የሐሰት ሃይማኖት ይህንን የነገሮች ሥርዓት ለመታደግ ምን ሊያደርገው የሚችለው ነገር አለ?

      28 “የግብጽም መንፈስ በውስጥዋ ባዶ ይሆናል፣ ምክራቸውንም አጠፋለሁ፤ እነርሱም ጣዖቶቻቸውን በድግምት የሚጠነቁሉትንም መናፍስት ጠሪዎቻቸውንም ጠንቋዮቻቸውንም ይጠይቃሉ።” (ኢሳይያስ 19:​3) ሙሴ ፈርዖን ፊት በቀረበ ጊዜ የግብጽ ካህናት የይሖዋን ኃይል ሊገዳደሩ ባለመቻላቸው ኃፍረት ተከናንበዋል። (ዘጸአት 8:​18, 19፤ ሥራ 13:​8፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:​8) በተመሳሳይም በፍርድ ቀን የሐሰት ሃይማኖቶች ይህንን ብልሹ ሥርዓት ለመታደግ አይችሉም። (ከ⁠ኢሳይያስ 47:​1, 11-13 ጋር አወዳድር።) የኋላ ኋላ ግብጽ ‘ጨካኝ ጌታ ’ በሆነው በአሦር እጅ ወድቃለች። (ኢሳይያስ 19:​4) ይህም የአሁኑ የነገሮች ሥርዓት ለሚጠብቀው አስፈሪ የወደፊት ዕጣ ጥላ ይሆናል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ