የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ባቢሎን ወደቀች!’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 8. በትንቢት በተነገረው መሠረት ጠላቶቻቸው ከቅጥሩ ውጭ ሠፍረው የነበረ ቢሆንም ባቢሎናውያኑ ምን እያደረጉ ነበር?

      8 በዚያች የቁርጥ ቀን ምሽት ባቢሎናውያን ሽብር ይሆናል ብለው እንዲያስቡ የሚያደርጋቸው ምንም ነገር አይኖርም። ከሁለት መቶ ዓመታት ገደማ ቀደም ብሎ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል ተንብዮአል:- “ማዕዱን ያዘጋጃሉ፣ ምንጣፉንም ይዘረጋሉ፣ ይበሉማል፣ ይጠጡማል።” (ኢሳይያስ 21:​5ሀ) አዎን፣ ዕብሪተኛው ንጉሥ ብልጣሶር ትልቅ ግብዣ አዘጋጅቷል። በሺህ ለሚቆጠሩት መኳንንቱ እንዲሁም በጣም ብዙ ለሆኑት ሚስቶቹና ቁባቶቹ የሚሆን አዳራሽ ተነጥፏል። (ዳንኤል 5:​1, 2) እነዚህ በፈንጠዝያ የተጠመዱ ሰዎች የጠላት ሠራዊት ከቅጥሩ ውጭ እንዳለ ያውቃሉ። ይሁን እንጂ ከተማቸው ፈጽሞ የምትበገር እንዳልሆነች ተሰምቷቸዋል። ግዙፍ ቅጥሯና ጥልቅ የሆነው የውኃ ቦይ ከተማቸው በጠላት እጅ እንዳትወድቅ ይከላከላል። ስፍር ቁጥር የሌላቸው አማልክቶቿስ የት ሄደው። ስለዚህ “ይበሉማል፤ ይጠጡማል።” ብልጣሶር የጠጣው መጠጥ ራሱ ላይ ወጣ። የሰከረው ግን እርሱ ብቻ አይመስልም። ቀጥሎ ካሉት የኢሳይያስ ትንቢታዊ ቃላት መረዳት እንደሚቻለው ከፍተኛ ባለ ሥልጣናቱ ከነበሩበት የስካር ድንዛዜ የሚያባንናቸው ነገር አስፈልጎ ነበር።

      9. ‘ጋሻውን መቀባት’ ያስፈለገው ለምንድን ነው?

      9 “እናንተ መሳፍንት ሆይ፣ ተነሡ፣ ጋሻውን አዘጋጁ [“ቀቡ፣” NW ]።” (ኢሳይያስ 21:​5ለ) ፈንጠዝያው ድንገት ተቋረጠ። መሳፍንቱ ለመንቃት ተገደዱ! አረጋዊው ነቢይ ዳንኤል ተጠርቶ ሲመጣ ይሖዋ፣ ኢሳይያስ በተናገረው መሠረት የባቢሎኑን ንጉሥ ብልጣሶርን እንዴት ሽብር ላይ እንደጣለው በግልጽ ተመልክቷል። የሜዶን፣ የፋርስና የኤላማውያን ጥምር ኃይል የከተማዋን መከላከያ ደርምሶ ሲገባ የንጉሡ መኳንንት በግራ መጋባት ስሜት ተዋጡ። ባቢሎን ቅጽበታዊ አወዳደቅ ወደቀች! ይሁንና “ጋሻውን ቀቡ” የሚለው አነጋገር ምንን የሚያመለክት ነው? የአንድ ብሔር ንጉሥ ምድሪቱን የሚከላከልና የሚጠብቅ በመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ንጉሡን እንደ ጋሻ አድርጎ የሚጠቅስበት ጊዜ አለ።b (መዝሙር 89:​18 NW ) በመሆኑም ይህ የኢሳይያስ ጥቅስ አዲስ ንጉሥ እንደሚያስፈልግ እየተነበየ እንዳለ እሙን ነው። ለምን? ምክንያቱም ብልጣሶር “በዚያ ሌሊት” ተገድሏል። በዚህ መንገድ ‘ጋሻውን መቀባት’ ወይም አዲስ ንጉሥ መሾም አስፈልጎ ነበር።​—⁠ዳንኤል 5:​1-9, 30

  • ‘ባቢሎን ወደቀች!’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • b ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች “ጋሻውን ቀቡ” የሚለው አነጋገር የሚያመለክተው የቆዳ ጋሻዎች የሚወረወሩትን አብዛኛዎቹን ፍላጻዎች እንዲያንሸራትቱ ሲባል ከውጊያው በፊት በዘይት ይቀቡ የነበረበትን ጥንታዊ ልማድ ነው ይላሉ። ይህ ፍቺ ትክክል ሊሆን ቢችልም ከተማዋ በወደቀችበት በዚያ ዕለት ምሽት ግን ባቢሎናውያን ጋሻቸውን ዘይት በመቀባት ለጦርነት የሚዘጋጁበት ይቅርና የሚዋጉበት ጊዜ እንኳን እንዳልነበራቸው ልብ ሊባል ይገባል!

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ