-
ከጠባቂው ጋር ተባብሮ ማገልገልመጠበቂያ ግንብ—2000 | ጥር 1
-
-
6. በትንቢት የተነገረለት ይሖዋ ያቆመው ጠባቂ ያወጀው ምሥራች ምንድን ነው? ይህስ ፍጻሜውን ያገኘው መቼ ነበር?
6 ይህ ለሐሰት ሃይማኖት እንዴት ያለ ታላቅ ድል ነበር! ይሁን እንጂ የባቢሎን የበላይነት ብዙም አልቆየ። ከ200 ዓመታት በፊት ግን ይሖዋ “ሂድ ጉበኛም አቁም፣ የሚያየውንም ይናገር” የሚል ትእዛዝ ሰጥቷል። ይህ ጉበኛ መናገር ያለበት መልእክት ምን ነበር? “ባቢሎን ወደቀች ወደቀች፣ የተቀረጹም የአማልክቶችዋ ምስሎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ” የሚል ነው። (ኢሳይያስ 21:6, 9) ደግሞም በ539 ከዘአበ ትንቢታዊው ቃል በትክክል ፍጻሜውን አግኝቷል። ኃያሏ ባቢሎን በመውደቋ የአምላክ የቃል ኪዳን ሕዝብ ወዲያው ወደ ትውልድ አገሩ ለመመለስ በቅቷል።
-
-
ከጠባቂው ጋር ተባብሮ ማገልገልመጠበቂያ ግንብ—2000 | ጥር 1
-
-
13. (ሀ) ይሖዋ ያቆመው ጠባቂ ያወጀው መልእክት ምንድን ነው? (ለ) ታላቂቱ ባቢሎን ወድቃለች ሊባል የሚችለው እንዴት ነው?
13 ይህ ጠባቂ ያየው ነገር ምን ነበር? ይሖዋ ያቆመው ጠባቂ ማለትም የምሥክሮቹ ቡድን “ባቢሎን ወደቀች ወደቀች፣ የተቀረጹም የአማልክቶችዋ ምስሎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ!” ሲል በድጋሚ አውጆአል። (ኢሳይያስ 21:9) በዚህ ጊዜ አንደኛውን የዓለም ጦርነት ተከትሎ ከመንበረ ሥልጣንዋ የተወገደችው የዓለም የሐሰት ሃይማኖት ግዛት የሆነችው ታላቂቱ ባቢሎን ናት። (ኤርምያስ 50:1-3፤ ራእይ 14:8) ይህ ምንም አያስገርምም! ታላቁ ጦርነት የተባለለት ይህ ውጊያ የተጀመረው በሕዝበ ክርስትና አገሮች ውስጥ ሲሆን በሁለቱም ወገን የነበሩት ቀሳውስት ለጋ ወጣቶች በጦርነት እሳት ውስጥ እንዲማገዱ በመቀስቀስ እሳቱ ይበልጥ እንዲፋፋም አድርገዋል። እንዴት ያለ አሳፋሪ ተግባር ነው! በ1919 በወቅቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ተብለው ይታወቁ የነበሩት የይሖዋ ምሥክሮች ከነበሩበት እንቅስቃሴ አልባ ሁኔታ ተነሥተው እስከ ዛሬም ድረስ የቀጠለውን ምድር አቀፍ የምሥክርነት ዘመቻ ሲያጧጡፉ ታላቂቱ ባቢሎን ልትገታቸው አልቻለችም። (ማቴዎስ 24:14) በስድስተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ የእስራኤላውያኑ ነፃ መውጣት የባቢሎንን ውድቀት የሚያሳይ እንደነበር ሁሉ ይህም የታላቂቱን ባቢሎን ውድቀት የሚያበስር ነበር።
-