የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከዳተኛነትን የሚመለከት የማስጠንቀቂያ ትምህርት
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 6. (ሀ) በኢየሩሳሌም ውስጥ ምን ዓይነት ሁኔታ ነግሦ ነበር? (ለ) አንዳንዶች የፈነጠዙት ለምንድን ነው? ይሁንና ምን ይጠብቃቸዋል?

      6 ኢሳይያስ እንዲህ በማለት ይቀጥላል:- “ጩኸትና ፍጅት የተሞላብሽ ከተማ፣ ደስታ ያለሽ ከተማ ሆይ፣ በአንቺ ውስጥ የተገደሉት በሰይፍ የተገደሉ አይደሉም፣ በሰልፍም የሞቱ አይደሉም።” (ኢሳይያስ 22:​2) ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ ከተማዋ በመጉረፋቸው ከተማዋ ተተረማምሳለች። በጎዳና ላይ የሚሄዱትም ሰዎች ይንጫጫሉ እንዲሁም ተሸብረዋል። አንዳንዶች ግን ምናልባት አስተማማኝ ሁኔታ እንዳላቸው ወይም ስጋቱ እንዳለፈ ስለተሰማቸው ሊሆን ይችላል ፈንጥዘዋል።a ይሁን እንጂ በዚህ ጊዜ መፈንጠዝ ሞኝነት ነው። ብዙዎቹ የከተማዋ ነዋሪዎች በሰይፍ ስለት ከመገደል የከፋ አሟሟት ይጠብቃቸዋል። ዙሪያዋን የተከበበች ከተማ ከውጭ ምግብ ማግኘት የምትችልበት መንገድ ሁሉ ይዘጋል። በከተማዋ ውስጥ ያለው ክምችት እየተመናመነ ይሄዳል። ረሃቡና መጨናነቁ ለወረርሽኝ በር ይከፍታል። ከዚህ የተነሣ በኢየሩሳሌም ያሉ ብዙዎች በረሃብና በቸነፈር ይሞታሉ። ይህ ነገር በ607 ከዘአበ እና በ70 እዘአ ተከስቷል።​—⁠2 ነገሥት 25:​3፤ ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:​9, 10b

  • ከዳተኛነትን የሚመለከት የማስጠንቀቂያ ትምህርት
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • a በ66 እዘአ ኢየሩሳሌምን ከብቦ የነበረው የሮማ ሠራዊት ወደኋላ ሲያፈገፍግ ብዙ አይሁዳውያን በደስታ ፈንጥዘው ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ