-
ከዳተኛነትን የሚመለከት የማስጠንቀቂያ ትምህርትየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
10. ለከተማዋ መጥፎ የሚሆነው ምን ከሆነ ነው?
10 ኢሳይያስ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል:- “መልካሞቹንም ሸለቆችሽን ሰረገሎች ሞሉባቸው፣ ፈረሰኞችም መቆሚያቸውን በበር ላይ አደረጉ። የይሁዳንም መጋረጃ ገለጠ።” (ኢሳይያስ 22:7, 8ሀ) ከኢየሩሳሌም ውጭ ያለውን ሜዳ ሠረገሎችና ፈረሶች ያጨናነቁት ሲሆን በከተማዋ በሮች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል። የሚገለጠው ‘የይሁዳ መጋረጃ’ ምንድን ነው? የከተማዋ በር ሳይሆን አይቀርም። የከተማዋ በር ተያዘ ማለት ከተማዋን የሚከላከሉት ሰዎች አበቃላቸው ማለት ይሆናል።c ይህ የመከላከያ መጋረጃ ሲገለጥ ከተማዋ ለወራሪዎቹ ክፍት ትሆናለች።
-
-
ከዳተኛነትን የሚመለከት የማስጠንቀቂያ ትምህርትየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
11, 12. የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ምን የመከላከል እርምጃ ወስደዋል?
11 አሁን ደግሞ ኢሳይያስ ሕዝቡ ራሳቸውን ከጠላት ለመከላከል ባደረጉት ጥረት ላይ ያተኩራል። መጀመሪያ የመጣላቸው ነገር በጦር መሣሪያ መጠቀም ነበር! “በዚያም ቀን በዱር ቤት የነበረውን የጦር ዕቃ ተመለከትህ፣ የዳዊትም ከተማ ፍራሾች እንደ በዙ አይታችኋል፣ የታችኛውንም ኩሬ ውኃ አከማችታችኋል።” (ኢሳይያስ 22:8ለ, 9) በዱር ቤት በነበረው የጦር ግምጃ ቤት ውስጥ መሣሪያዎች ተከማችተው ነበር። ይህን የጦር ግምጃ ቤት የገነባው ሰሎሞን ነው። የተገነባው ከሊባኖስ በመጣ ዝግባ ስለነበር “የሊባኖስ የዱር ቤት” ሊባል በቅቷል። (1 ነገሥት 7:2-5) ግድግዳዎቹ ተሰንጥቀው ክፍተት እንደፈጠሩ አስተውለዋል። ሕዝቡ ውኃ በማከማቸት ትልቅ ግምት የሚሰጠው አንድ የመከላከል እርምጃ ወስደዋል። የሕዝቡን ሕይወት ለማቆየት ውኃ አንገብጋቢ ነገር ነው። አንድ ከተማ ያለ ውኃ ልትቆም አትችልም። ያም ሆኖ ግን ይሖዋ ነፃ እንዲያወጣቸው እርሱን ስለመፈለጋቸው የተጠቀሰ አንድም ነገር እንደሌለ ልብ በል። ከዚህ ይልቅ የተመኩት ራሳቸው ባላቸው ነገር ነበር። እኛም ተመሳሳይ ስህተት እንዳንሠራ እንጠንቀቅ!—መዝሙር 127:1
-
-
ከዳተኛነትን የሚመለከት የማስጠንቀቂያ ትምህርትየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
c ወይም ደግሞ ‘የይሁዳ መጋረጃ’ የሚለው መግለጫ የሚያመለክተው ከተማዋን ለመከላከል የሚያስችልን ሌላ ዝግጅት ምናልባትም ጦር መሣሪያ የሚከማችበትንና ወታደሮች የሚጠብቁበት ምሽግ ሊሆን ይችላል።
-