የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከዳተኛነትን የሚመለከት የማስጠንቀቂያ ትምህርት
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 19, 20. (ሀ) ኤልያቄም ለሕዝቡ በረከት የሆነው እንዴት ነው? (ለ) በሳምናስ መታመናቸውን የሚቀጥሉ ሰዎች ምን ያገኛሉ?

      19 በመጨረሻም ይሖዋ ምሳሌያዊ አገላለጽ በመጠቀም ሥልጣኑ ከሳምናስ ወደ ኤልያቄም ማሸጋገሩን እንዲህ በማለት ይገልጻል:- “በታመነም ስፍራ [ኤልያቄምን] እንደ ችንካር እተክለዋለሁ፣ ለአባቱም ቤት የክብር ዙፋን ይሆናል። የአባቱንም ቤት ክብር ሁሉ ልጆቹንም የልጅ ልጆቹንም፣ ከጽዋ ዕቃ ጀምሮ እስከ ማድጋ ዕቃ ድረስ፣ ታናናሹን ዕቃ ሁሉ ይሰቅሉበታል። በዚያ ቀን፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በታመነው ስፍራ የተተከለው ችንካር [ሳምናስ] ይወልቃል፤ ተሰብሮም ይወድቃል፣ በእርሱም ላይ የተሰቀለው ሸክም ይጠፋል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።”​—⁠ኢሳይያስ 22:​23-25

      20 በእነዚህ ቁጥሮች ላይ የተጠቀሰው የመጀመሪያው ችንካር ኤልያቄም ነው። ለአባቱ የኬልቅያስ ቤት “የክብር ዙፋን” ይሆናል። ሳምናስ እንዳደረገው የአባቱን ቤት ክብር አያዋርድም ወይም አያሰድብም። ኤልያቄም የቤቱ ዕቃ ሁሉ የሚሰቀልበት አስተማማኝ መንጠልጠያ ማለትም የንጉሡ አገልጋዮች ሁሉ የሚታመኑበት ሰው ይሆናል። (2 ጢሞቴዎስ 2:​20, 21) ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ ሁለተኛው ችንካር የሚያመለክተው ሳምናስን ነው። አስተማማኝ መስሎ ቢታይም ከቦታው ይወገዳል። እርሱን ተስፋ የሚያደርጉ ሁሉ ይወድቃሉ።

  • ከዳተኛነትን የሚመለከት የማስጠንቀቂያ ትምህርት
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • [በገጽ 239 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

      ሕዝቅያስ ኤልያቄምን ‘በአስተማማኝ ስፍራ እንዳለ ችንካር’ አድርጎታል

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ