-
ይሖዋ የጢሮስን ትዕቢት ይሽራልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
16, 17. ከተማዋ ስትወድቅ የጢሮስ ነዋሪዎች ምን ይሆናሉ? (የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት።)
16 ይሖዋ ስለ ጢሮስ የተናገረውን የውግዘት ቃል በመቀጠል ኢሳይያስ እንዲህ ይላል:- “የተርሴስ ልጅ ሆይ፣ የሚከለክልሽ የለምና እንደ ዓባይ ወንዝ በአገርሽ ላይ ጐርፈሽ እለፊ። በባሕር ላይ እጁን ዘረጋ መንግሥታትንም አናወጠ፤ ምሽጎችዋንም ያጠፉ ዘንድ እግዚአብሔር ስለ ከነዓን [“ፊንቄ፣” NW] አገር አዘዘ። እርሱም:- አንቺ የተበደልሽ የሲዶና ድንግል ልጅ ሆይ፣ ከእንግዲህ ወዲህ ደስ አይበልሽ፤ ተነሥተሽ ወደ ኪቲም ተሻገሪ፣ በዚያም ደግሞ አታርፊም አለ።”—ኢሳይያስ 23:10-12
-
-
ይሖዋ የጢሮስን ትዕቢት ይሽራልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
18. ጢሮስ “የሲዶና ድንግል ልጅ” ተብላ የተጠራችው ለምንድን ነው? ያለችበት ሁኔታስ የሚለወጠው እንዴት ነው?
18 ኢሳይያስ ጢሮስን “የሲዶና ድንግል ልጅ” ሲልም ጠርቷታል። ይህም ከዚህ ቀደም በባዕድ ወራሪዎች ተይዛና ተበዝብዛ እንደማታውቅ አሁንም ቢሆን ነፃ ግዛት መሆኗን የሚጠቁም ነው። (ከ2 ነገሥት 19:21፤ ኢሳይያስ 47:1፤ ኤርምያስ 46:11 ጋር አወዳድር።) ይሁንና፣ አሁን ግን ጢሮስ ትጠፋለች። አንዳንዶቹ ነዋሪዎቿም ልክ እንደ ስደተኛ የፊንቄ ቅኝ ግዛት ወደ ሆነችው ኪቲም ይሻገራሉ። ሆኖም ኢኮኖሚያዊ ኃይላቸው ስለተሟጠጠ በኪቲም እረፍት አያገኙም።
-