የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ ንጉሥ ነው
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 13, 14. (ሀ) ይሖዋ ስለ መከር አሰባሰብ ያወጣቸው ሕጎች ምንድን ናቸው? (ለ) ኢሳይያስ ከይሖዋ ፍርድ በሕይወት የሚተርፉ ሰዎች እንዳሉ ለማስረዳት ስለ መከር አሰባሰብ የሰጠውን ሕግ እንደ ምሳሌ አድርጎ የተጠቀመበት እንዴት ነው? (ሐ) ከፊታቸው መከራ የሞላባቸው የጨለማ ወቅቶች ይጠብቋቸው የነበረ ቢሆንም የታመኑ አይሁዳውያን ስለ ምን ነገር እርግጠኛ መሆን ይችሉ ነበር?

      13 እስራኤላውያን የወይራ ፍሬ ለመሰብሰብ ፍሬው እንዲረግፍላቸው ዛፉን በበትር ይመቱ ነበር። የአምላክ ሕግ የቀሩትን ፍሬዎች ለመልቀም ወደ ቅርንጫፎቹ እንዳይወጡ ይከለክላቸው ነበር። የወይን ፍሬያቸውንም ከሰበሰቡ በኋላ የቀረውን ለመልቀም መመለስ አልነበረባቸውም። ከመከሩ የቀረውን ፍሬ ለድሆች ማለትም “ለመጻተኛና ለድሀ አደግ ለመበለትም” ቃርሚያ መተው ነበረባቸው። (ዘዳግም 24:​19-21) ኢሳይያስ እነዚህን በሚገባ የሚታወቁ ሕግጋት መሠረት በማድረግ ከይሖዋ ፍርድ በሕይወት የሚተርፉ ሰዎች ስለመኖራቸው የሚገልጸውን የሚያጽናና እውነታ በምሳሌ አስረድቷል:- “የወይራን ዛፍ እንደ መምታት፣ ከወይንም መከር በኋላ ቃርሚያውን እንደ መልቀም፣ እንዲሁ በምድር መካከል በአሕዛብም መካከል ይሆናል። እነዚህ ድምፃቸውን ያነሣሉ፣ እልልም ይላሉ፣ ስለ እግዚአብሔር ክብርም ከባሕር ይጣራሉ። ስለዚህ እግዚአብሔርን በምሥራቅ [“በብርሃን ምድር፣” NW]፣ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርንም ስም በባሕር ደሴቶች አክብሩ። ለጻድቁ ክብር ይሁን የሚለውን ዝማሬ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል።”​—⁠ኢሳይያስ 24:​13-16ሀ

      14 ከመከር በኋላ በዛፉ ወይም በወይኑ ተክል ላይ የሚቀር ፍሬ እንደነበረ ሁሉ ይሖዋ የፍርድ እርምጃውን ከወሰደ በኋላ “ከወይንም መከር በኋላ ቃርሚያውን እንደ መልቀም” ያህል የሚቀሩ ጥቂቶች ይኖራሉ። በቁጥር 6 ላይ እንደተጠቀሰው ነቢዩ “ጥቂት ሰዎች ይቀራሉ” በማለት ስለ እነዚሁ ሰዎች ተናግሯል። ምንም ጥቂት ቢሆኑ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ከሚመጣው ጥፋት የሚተርፉ ሰዎች ይኖራሉ። ከጊዜ በኋላም ቀሪዎች ከምርኮ ተመልሰው በምድሪቱ መኖር ይጀምራሉ። (ኢሳይያስ 4:​2, 3፤ 14:​1-5) ቅን የሆኑ ሰዎች ጨለማ የሆነ የፈተና ወቅት የሚገጥማቸው ቢሆንም ከፊታቸው የነፃነትና የደስታ ጊዜ እንደሚጠብቃቸው እርግጠኛ ሊሆኑ ይችላሉ። በሕይወት የሚተርፉት ሰዎች የይሖዋ ትንቢታዊ ቃል ፍጻሜውን ሲያገኝ ከመመልከታቸውም ሌላ ኢሳይያስ እውነተኛ የአምላክ ነቢይ እንደነበረ ይገነዘባሉ። ስለ መልሶ መቋቋም የተነገረው ትንቢት ፍጻሜውን ሲያገኝ በዓይናቸው በማየታቸው በደስታ ይፈነድቃሉ። ከሜድትራኒያን የባሕር ደሴቶች፣ ‘በብርሃን ምድር’ (በፀሐይ መውጫ፣ በምሥራቅ) ካለችው ባቢሎን ወይም ከሌላ ሩቅ ቦታም ቢሆን ከየተበታተኑበት “ለጻድቁ ክብር ይሁን” በሚል ዝማሬ አምላክን ያወድሳሉ!

  • ይሖዋ ንጉሥ ነው
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 15, 16. (ሀ) ኢሳይያስ በሕዝቡ ላይ ስለሚደርሰው ነገር ሲያስብ ምን ተሰምቶታል? (ለ) ታማኝ ያልሆኑት የምድሪቱ ነዋሪዎች ምን ይገጥማቸዋል?

      15 አሁን ግን የሚደሰቱበት ጊዜ አይደለም። ኢሳይያስ በዘመኑ የነበሩትን ሰዎች በወቅቱ ወደ ነበረው ሁኔታ ሲመልሳቸው እንዲህ ብሏል:- “እኔ ግን:- ከሳሁ፣ ከሳሁ፣ ወዮልኝ! ወንጀለኞች ወንጅለዋል፤ ወንጀለኞች እጅግ ወንጅለዋል አልሁ። በምድር ላይ የምትኖር ሆይ፣ ፍርሃትና ገደል ወጥመድም በአንተ ላይ አሉ። የሰማይ መስኮቶች ተከፍተዋልና፣ የምድርም መሠረት ተናውጣለችና ከፍርሃት ድምፅ የሸሸ በገደል ይወድቃል፣ ከገደልም የወጣ በወጥመድ ይያዛል። ምድር ተሰባበረች፣ ምድር ፈጽማ ደቀ​ቀች፣ ምድር ተነዋወጠች። ምድር እንደ ሰካር ሰው ትንገደገዳለች፣ እንደ ዳስም ትወዛወዛለች፤ መተላለፍዋ ይከብድባታል፣ ትወድቅማለች ደግ​ማም አትነሣም።”​—⁠ኢሳይያስ 24:​16ለ-20

      16 ኢሳይያስ በሕዝቡ ላይ በሚደርሰው ነገር እጅግ አዝኗል። በዙሪያው ያለው ነገር ሕመምና ወዮታ አስከትሎበታል። ወንጀለኞች በዝተው የምድሪቱን ነዋሪ እያስጨነቁት ነው። ይሖዋ ጥበ​ቃውን ሲያነሳ ከዳተኛ የሆኑት የይሁዳ ነዋሪዎች ቀን ከሌት የስጋት ኑሮ ለመምራት ይገደ⁠ዳሉ። ለሕይወታቸው ዋስትና አይኖራቸውም። የይሖዋን ትእዛዛት በመተዋቸውና አምላካዊውን ጥበብ ቸል በማለታቸው ምክንያት ከሚደርስባቸው ቅጣት የሚያመል​ጡበት ቀዳዳ የለም። (ምሳሌ 1:​24-27) ምንም እንኳ በምድሪቱ ያሉ ወንጀለኞች ሕዝቡን በሐሰትና በማታለል ወደ ጥፋት ለመምራት ምንም ችግር እንደሌለ ሊያሳምኑት ቢሞክሩም ጥፋት መምጣቱ አይቀርም። (ኤርምያስ 27:​9-15) ጠላት ከውጭ መጥቶ ይበዘብዛቸዋል፤ በምርኮም ያግዛቸዋል። ይህ ሁሉ ነገር ኢሳይያስን አስጨንቆታል።

  • ይሖዋ ንጉሥ ነው
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • [በገጽ 267 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

      ኢሳይያስ ሕዝቡ ስለሚጠብቀው ዕጣ ሲያስብ እጅግ አዝኗል

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ