የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ ንጉሥ ነው
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 15, 16. (ሀ) ኢሳይያስ በሕዝቡ ላይ ስለሚደርሰው ነገር ሲያስብ ምን ተሰምቶታል? (ለ) ታማኝ ያልሆኑት የምድሪቱ ነዋሪዎች ምን ይገጥማቸዋል?

      15 አሁን ግን የሚደሰቱበት ጊዜ አይደለም። ኢሳይያስ በዘመኑ የነበሩትን ሰዎች በወቅቱ ወደ ነበረው ሁኔታ ሲመልሳቸው እንዲህ ብሏል:- “እኔ ግን:- ከሳሁ፣ ከሳሁ፣ ወዮልኝ! ወንጀለኞች ወንጅለዋል፤ ወንጀለኞች እጅግ ወንጅለዋል አልሁ። በምድር ላይ የምትኖር ሆይ፣ ፍርሃትና ገደል ወጥመድም በአንተ ላይ አሉ። የሰማይ መስኮቶች ተከፍተዋልና፣ የምድርም መሠረት ተናውጣለችና ከፍርሃት ድምፅ የሸሸ በገደል ይወድቃል፣ ከገደልም የወጣ በወጥመድ ይያዛል። ምድር ተሰባበረች፣ ምድር ፈጽማ ደቀ​ቀች፣ ምድር ተነዋወጠች። ምድር እንደ ሰካር ሰው ትንገደገዳለች፣ እንደ ዳስም ትወዛወዛለች፤ መተላለፍዋ ይከብድባታል፣ ትወድቅማለች ደግ​ማም አትነሣም።”​—⁠ኢሳይያስ 24:​16ለ-20

  • ይሖዋ ንጉሥ ነው
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 17. (ሀ) ማምለጥ የማይቻለው ለምንድን ነው? (ለ) የይሖዋ የቅጣት ኃይል ከሰማይ ሲገለጥ ምድሪቱ ምን ትሆናለች?

      17 ይሁንና ነቢዩ ምንም ማምለጫ እንደሌለ የመናገር ግዴታ ነበረበት። ሰዎች በየትም አቅጣጫ ለማምለጥ ቢሞክሩ ይያዛሉ። አንዳንዶች አንዱን ችግር ያመልጡ ይሆናል። ይሁን እንጂ ሌላ ችግር ላይ ይወድቃሉ። ምንም አስተማማኝ ሁኔታ አይኖርም። ሁኔታው ከአንዱ ወጥመድ አምልጦ ሌላ ወጥመድ ውስጥ ከሚወድቅ የሚታደን እንስሳ የተለየ አይሆንም። (ከ⁠አሞጽ 5:​18, 19 ጋር አወዳድር።) የይሖዋ የቅጣት ኃይል ከሰማይ በመገለጥ የምድሪቱን መሠረት ያናጋል። ምድሪቱ ከኃጢአቷ ክብደት የተነሣ እንደሰከረ ሰው ትውተረተርና ትወድቃለች። እንደገና መነሳትም አትችልም። (አሞጽ 5:​2) ይሖዋ የሚሰጠው ፍርድ የመጨረሻ ይሆናል። ምድሪቱ ፍጹም ጥፋትና ውድመት ይጠብቃታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ