-
የይሖዋ እጅ ከፍ ከፍ ትላለችየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
‘ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን የሰባ ግብዣ’
6, 7. (ሀ) ይሖዋ ምን ዓይነት ግብዣ አዘጋጅቷል? የተዘጋጀውስ ለእነማን ነው? (ለ) ኢሳይያስ በትንቢት የተናገረለት የሰባ ግብዣ የምን ነገር ጥላ ነው?
6 ይሖዋ በተለይ በመንፈሳዊ ነገሮች ረገድ ልክ እንደ አንድ አፍቃሪ አባት ልጆቹን ከአደጋ ከመጠበቅም አልፎ ይመግባቸዋል። በ1919 ሕዝቡን ነፃ ካወጣ በኋላ የሰባ የድል ግብዣ ማለትም የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ አዘጋጅቶላቸዋል:- “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፣ ያረጀ የወይን ጠጅ፣ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፣ የጥሩና ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።”—ኢሳይያስ 25:6
7 ይህ የሰባ ግብዣ የቀረበው በይሖዋ “ተራራ” ላይ ነው። ይህ ተራራ ምንድን ነው? “በዘመኑ ፍጻሜ” ‘አሕዛብ ሁሉ የሚጎርፉበት የእግዚአብሔር ቤት ተራራ’ ነው። የታመኑት አምላኪዎቹ ሌሎችን የማይጎዱበትና የማያጠፉበት ‘የተቀደሰው የይሖዋ ተራራ’ ነው። (ኢሳይያስ 2:2፤ 11:9) ይሖዋ በዚህ ከፍ ያለ የአምልኮ ሥፍራ የታመኑ ሆነው ለተገኙት ሰዎች ሁሉም ነገር የተትረፈረፈበትን የሰባ ግብዣ ያቀርባል። በአሁኑ ጊዜ ተትረፍርፈው የሚቀርቡት መልካም መንፈሳዊ ዝግጅቶች የአምላክ መንግሥት ብቸኛ የሰው ልጅ መስተዳድር በሚሆንበት ጊዜ ለሚኖሩት መልካም ሰብዓዊ ነገሮች ጥላ ይሆናሉ። በዚያ ጊዜ ረሃብ አይኖርም። ‘በምድሩ ላይ በቂ እህል ይኖራል። ተራሮች በሰብል ይሸፈናሉ።’—መዝሙር 72:8, 16 የ1980 ትርጉም
8, 9. (ሀ) ከምድር ገጽ የሚወገዱት ሁለቱ የሰው ልጅ ጠላቶች የትኞቹ ናቸው? አብራራ። (ለ) አምላክ የሕዝቡን ስድብ ለማስወገድ ምን እርምጃ ይወስዳል?
8 በአሁኑ ጊዜ አምላክ ከሚያቀርበው መንፈሳዊ ድግስ የሚቋደሱ ሰዎች ወደፊት ክብራማ ተስፋ ይጠብቃቸዋል። ቀጥሎ ኢሳይያስ የተናገረውን ነገር ልብ በል። ኃጢአትና ሞትን ‘ከመጋረጃ’ እና ‘ከመሸፈኛ’ ጋር በማነፃፀር እንዲህ ብሏል:- “በዚህም ተራራ ላይ [ይሖዋ ] በወገኖች ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፣ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል። ሞትን ለዘላለም ይውጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል።”—ኢሳይያስ 25:7, 8ሀ
-
-
የይሖዋ እጅ ከፍ ከፍ ትላለችየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
[በገጽ 275 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
“ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች”
-