የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘አሁን የአምላክ ሕዝብ ናችሁ’
    መጠበቂያ ግንብ—2014 | ኅዳር 15
    • 17, 18. (ሀ) ጎግ በይሖዋ ሕዝቦች ላይ ጥቃት በሚሰነዝርበት ወቅት ምን መመሪያ ይሰጠናል? (ለ) የይሖዋን ጥበቃ ማግኘት ከፈለግን ምን ማድረግ ይኖርብናል?

      17 ጎግ ጥቃት መሰንዘር ሲጀምር ይሖዋ “ሕዝቤ ሆይ፤ ሂድ ወደ ቤትህ ግባ፤ በርህን ከኋላህ ዝጋ፤ ቍጣው እስኪያልፍ ድረስ፣ ለጥቂት ቀን ተሸሸግ” በማለት ለአገልጋዮቹ መመሪያ ይሰጣቸዋል። (ኢሳ. 26:20) በዚያ ወሳኝ ጊዜ ይሖዋ ሕይወታችንን ለማዳን የሚያስችል መመሪያ ይሰጠናል፤ በኢሳይያስ ትንቢት ላይ “ቤት” የሚለው አገላለጽ ከጉባኤያችን ጋር የተያያዙ ዝግጅቶችን ሊያመለክት ይችላል።

      18 እንግዲያው በታላቁ መከራ ወቅት ይሖዋ ካዘጋጀው ጥበቃ ጥቅም ለማግኘት ከፈለግን ይሖዋ በምድር ላይ ሕዝብ እንዳለውና እነሱንም በጉባኤዎች እንዳደራጃቸው መገንዘብ አለብን። ከይሖዋ ሕዝብ ጋር መተባበራችንን መቀጠል ይኖርብናል፤ እንዲሁም ከጉባኤያችን መራቅ የለብንም። እኛም እንደ መዝሙራዊው “ማዳን የእግዚአብሔር [“የይሖዋ፣” NW] ነው፤ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን” በማለት በሙሉ ልባችን እናውጅ።—መዝ. 3:8

  • ‘አሁን የአምላክ ሕዝብ ናችሁ’
    መጠበቂያ ግንብ—2014 | ኅዳር 15
አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ