የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • እንግዳ ስለሆነው የይሖዋ ሥራ ማስጠንቀቃችሁን ቀጥሉ
    መጠበቂያ ግንብ—1991 | ሰኔ 1
    • 17, 18. ይሖዋ ለሕዝቡ የጌጥ አክሊልና የውበት አበባ ጉንጉን የሆነው እንዴት ነው?

      17 ነቢዩ ኢሳይያስ ለንጹሕ አምልኰ ቆራጥ አቋም የሚወስዱትን ሰዎች ደስተኛ ሁኔታ ይገልጽልናል። እንዲህ ይላል፦ “በዚያ ቀን የሠራዊት ጌታ [ይሖዋ (አዓት)] ለቀሩት ሕዝቡ የክብር ዘውድና የጌጥ አክሊል ይሆናል። በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጥም የፍርድ መንፈስ ሰልፉን [ከበር] ለሚመልሱም ኃይል ይሆናል።”​—ኢሳይያስ 28:5, 6

  • እንግዳ ስለሆነው የይሖዋ ሥራ ማስጠንቀቃችሁን ቀጥሉ
    መጠበቂያ ግንብ—1991 | ሰኔ 1
    • 19. በፍርድ ወንበር ላይ የተቀመጠው ማነው? ይሖዋ ለሱ የፍትሕ መንፈስ የሆነለትስ እንዴት ነው?

      19 “በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጠው” ለኢየሱስ ይሖዋ “የፍርድ (የፍትህ) መንፈስ” ሆኖለታል። ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ በሚያሰክር የዓለማዊ ኅብረት መንፈስ ሥር ለመውደቅ እምቢ አለ። ዛሬ በዙፋን የተቀመጠ የይሖዋ ንጉሥ እንደመሆኑ መጠን ትክክለኛና የተጣራ ውሣኔ እንዲያደርግ በሚመራው ቅዱስ መንፈስ ተሞልቷል። “የይሖዋ መንፈስ፣ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣ የምክርና የኃይል መንፈስ የእውቀትና ይሖዋን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል” የሚለው ትንቢት በኢየሱስ ላይ ተፈጽሟል። (ኢሳይያስ 11:2) በእውነትም ይሖዋ በኢየሱስ አማካኝነት ‘ፍትሕን የመሠረት መለኪያ ጽድቅን ደግሞ ቱንቢ ያደርጋል።’ (ኢሳይያስ 28:17) በመንፈሳዊ ሰካራም የሆኑ ጠላቶች በጥፋት ጎርፍ የሚዋጡ ሲሆን ለይሖዋ ቅዱስ ስምና ለጽንፈ ዓለማዊ ሉዓላዊነቱ ፍትሕ ይደረጋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ