-
ኢሳይያስ ይሖዋ ስለሚያከናውነው ‘እንግዳ ሥራ’ ይተነብያልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
8. ለኢሳይያስ መልእክት የተሰጠው ምላሽ ምን ነበር?
8 የይሁዳ መሪዎች ለይሖዋ ማስጠንቀቂያ የሚሰጡት ምላሽ ምንድን ነው? ኢሳይያስ እንደ ሕፃን እንደቆጠራቸው አድርገው በመክሰስ ያላግጡበታል:- “እውቀትን ለማን ያስተምረዋል? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? ወተትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን? ትእዛዝ በትእዛዝ፣ ትእዛዝ በትእዛዝ፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ነው።” (ኢሳይያስ 28:9, 10) ኢሳይያስ የሚናገረው ነገር ምንኛ ተደጋጋሚና እንግዳ ሆኖባቸው ነበር! በተደጋጋሚ ‘የይሖዋ ትእዛዝ ይህ ነው! የይሖዋ ትእዛዝ ይህ ነው! የይሖዋ ሥርዓት ይህ ነው! የይሖዋ ሥርዓት ይህ ነው!’ ይላቸው ነበር።a ይሁን እንጂ በቅርቡ ይሖዋ የይሁዳን ነዋሪዎች በተግባር ‘ያነጋግራቸዋል።’ ሌላ ቋንቋ የሚናገሩ ባዕድ ሰዎችን ማለትም የባቢሎንን ሠራዊት ይልክባቸዋል። ይህ ሠራዊት የይሖዋን “ትእዛዝ” በማስፈጸም ይሁዳን ያጠፋታል።—ኢሳይያስ 28:11-13ን አንብብ።
-
-
ኢሳይያስ ይሖዋ ስለሚያከናውነው ‘እንግዳ ሥራ’ ይተነብያልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
a በጥንቱ ዕብራይስጥ ውስጥ ኢሳይያስ 28:10 የተቀመጠው ለልጆች እንደሚነበነብ ቤት የሚመታ ግጥም ሆኖ ነበር። የኢሳይያስም መልእክት ለሃይማኖት መሪዎቹ ተደጋጋሚና የልጅ ሥራ ሆኖ ታይቷቸዋል።
-