-
ይሖዋ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉትን ያዋርዳልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
7 “የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን” እየመጣ ነው። በዚህ ጊዜ የአምላክ ቁጣ “በትዕቢተኛውና በኩራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፣ እርሱም ይዋረዳል፤ ደግሞም በረጅሙ ከፍ ባለውም በሊባኖስ ዝግባ ሁሉ ላይ፣ በረጅሙም ተራራ ሁሉ ላይ፣ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ፣ በረጅሙም ግንብ ሁሉ ላይ፣ በተመሸገውም ቅጥር ሁሉ ላይ፣ በተርሴስም መርከብ ሁሉ ላይ፣ በሚያማምሩ ጣዖታቱም ሁሉ ላይ ይሆናል።” (ኢሳይያስ 2:12-16) አዎን፣ የሰው ልጆች መኩራሪያ ሆኖ የቆመ የትኛውም ድርጅትም ሆነ አምላካዊ አክብሮት የሌለው እያንዳንዱ ግለሰብ በይሖዋ የቁጣ ቀን የእጁን ያገኛል። በዚህ መንገድ “ሰውም ሁሉ ይዋረዳል፣ የሰውም ኩራት ይወድቃል፣ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።”—ኢሳይያስ 2:17
8. አስቀድሞ የተነገረው የፍርድ ቀን በ607 ከዘአበ በኢየሩሳሌም ላይ የመጣው እንዴት ነው?
8 አስቀድሞ በትንቢት የተነገረለት የፍርድ ቀን በአይሁዳውያን ላይ የመጣው በ607 ከዘአበ የባቢሎኑ ንጉሥ ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን ባጠፋበት ጊዜ ነበር። ነዋሪዎቹ የተወደደችው ከተማቸው በእሳት ስትጋይ፣ ዕጹብ ድንቅ የሆኑት ሕንጻዎቻቸው ሲፈራርሱና ግዙፍ ቅጥሯ ሲደረማመስ ተመልክተዋል። የይሖዋም ቤተ መቅደስ ወደመ። ‘በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቀን’ መዝገባቸውም ሆነ ሠረገሎቻቸው ምንም ሊፈይዱ አልቻሉም። ጣዖቶቻቸውስ? ኢሳይያስ “ጣዖቶቻቸውም ሁሉ ፈጽመው ይጠፋሉ” ሲል አስቀድሞ የተናገረው ትንቢት በትክክል ተፈጽሟል። (ኢሳይያስ 2:18) መሳፍንቱንና ኃያላኖቻቸውን ጨምሮ አይሁዳውያን ወደ ባቢሎን በምርኮ ተወስደዋል። ኢየሩሳሌም ገና የ70 ዓመት ባድማነት ይጠብቃት ነበር።
-
-
ይሖዋ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉትን ያዋርዳልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
እያንዣበበ ያለው “የእግዚአብሔር ቀን”
10. ሐዋርያው ጳውሎስና ሐዋርያው ጴጥሮስ የተናገሩት ስለ የትኛው ‘የይሖዋ ቀን’ ነው?
10 ቅዱሳን ጽሑፎች በጥንቷ ኢየሩሳሌምና ይሁዳ ላይ ከመጣው የፍርድ ቀን እጅግ የላቀ ትርጉም ስለሚኖረው “የእግዚአብሔር ቀን” ይናገራሉ። ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ ተነሳስቶ ‘የይሖዋን ቀን መምጣት’ በዙፋን ላይ ከተቀመጠው ከኢየሱስ ክርስቶስ መገኘት ጋር በማዛመድ ተናግሯል። (2 ተሰሎንቄ 2:1, 2) ጴጥሮስ ደግሞ ይህንን ቀን ‘ጽድቅ ከሚኖርበት አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር’ መቋቋም ጋር አያይዞ ገልጾታል። (2 ጴጥሮስ 3:10-13) ይህ ቀን ይሖዋ ሕዝበ ክርስትናን ጨምሮ በመላው ክፉ የነገሮች ሥርዓት ላይ እርምጃ የሚወስድበት ቀን ነው።
11. (ሀ) መጪውን ‘የይሖዋ ቀን’ ‘የሚችለው ማን ነው?’ (ለ) ይሖዋን መጠጊያችን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
11 ነቢዩ ኢዩኤል “የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና ለቀኑ ወዮ! እርሱም ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል” ሲል ተናግሯል። ይህ “ቀን” ቅርብ ከመሆኑ አንጻር ሲታይ እያንዳንዱን ሰው የሚያሳስበው ነገር በዚህ አስፈሪ ጊዜ መሸሸጊያ ማግኘቱ ሊሆን አይገባምን? ኢዩኤል “ማንስ ይችለዋል?” ሲል ጠይቋል። “እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ . . . ይሆናል” በማለት ራሱ መልሱን ሰጥቷል። (ኢዩኤል 1:15፤ 2:11፤ 3:16) ይሖዋ አምላክ ትዕቢተኛ ለሆኑና ትምክህታቸውን በሀብት፣ በወታደራዊ ኃይል እንዲሁም በሰው ሠራሽ አማልክት ላይ ላደረጉ ሰዎች መሸሸጊያ ይሆናልን? በፍጹም ሊሆን አይችልም! አምላክ ተመሳሳይ ስህተት በመፈጸማቸው የራሱን የተመረጠ ሕዝብ እንኳ ትቷል። ሁሉም የአምላክ አገልጋዮች ‘ጽድቅንና ትሕትናን’ መፈለጋቸውና ለይሖዋ አምልኮ በሕይወታቸው ምን ቦታ እንደሰጡት በቁም ነገር ማሰባቸው ምንኛ አንገብጋቢ ነው!—ሶፎንያስ 2:2, 3
-