-
የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 23—ኢሳይያስ“ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 14
-
-
36 ኢሳይያስ በመቀጠል ንጉሥ የሚሆነውን መሲሕ እንዴት እንደገለጸ ተመልከት! ኢየሱስ፣ የይሖዋ ቅቡዕ መሆኑን ለማሳየት ስለተሰጠው ተልዕኮ የሚገልጸውን ክፍል ከኢሳይያስ ጥቅልል ላይ ካነበበ በኋላ “የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል” መስበኩን ቀጠለ፤ ይህን ያደረገበትንም ምክንያት ሲገልጽ “የተላክሁት ለዚሁ ዐላማ ነው” ብሏል። (ሉቃስ 4:17-19, 43፤ ኢሳ. 61:1, 2) አራቱ ወንጌሎች ስለ ኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎት እንዲሁም በኢሳይያስ ምዕራፍ 53 ላይ ስለተተነበየው የአሟሟቱ ሁኔታ በርካታ ዘገባዎችን በዝርዝር አስፍረዋል። አይሁዳውያን የመንግሥቱን ምሥራች ቢሰሙና የኢየሱስን ድንቅ ተአምራት ቢመለከቱም ልባቸው ደንዳና ስለነበር ትርጉሙ አልገባቸውም። ይህም የሆነው በኢሳይያስ 6:9, 10፤ 29:13 እና 53:1 ፍጻሜ መሠረት ነው። (ማቴ. 13:14, 15፤ ዮሐ. 12:38-40፤ ሥራ 28:24-27፤ ሮሜ 10:16፤ ማቴ. 15:7-9፤ ማር. 7:6, 7) በኢሳይያስ 8:14 እና 28:16 ፍጻሜ መሠረት ኢየሱስ ለእነርሱ የማሰናከያ ድንጋይ ቢሆንም ይሖዋ በጽዮን የተከለው መሠረትና መንፈሳዊ ቤቱን የሚገነባበት የማዕዘን ድንጋይ ሆኗል።—ሉቃስ 20:17፤ ሮሜ 9:32, 33፤ 10:11፤ 1 ጴጥ. 2:4-10
-
-
የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 60—1 ጴጥሮስ“ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 17
-
-
13 ጴጥሮስ አስፈሪ ችግሮችና ስደቶች ብቅ ብቅ ማለት በጀመሩበት ጊዜ ጥንካሬ የሚጨምር ማበረታቻ ሰጥቷል። ከዚህም በተጨማሪ መልእክቱ ዛሬም ቢሆን ተመሳሳይ ፈተና ለሚያጋጥማቸው ሁሉ ይህ ነው የማይባል ጠቃሚ ምክር ይዟል። ጴጥሮስ የይሖዋን ቃል በሚጠቅስበት ጊዜ የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍትን እንዴት እንደተጠቀመባቸው ልብ በል:- “እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።” (1 ጴጥ. 1:16፤ ዘሌ. 11:44) ከዚያም፣ በመንፈስ አነሳሽነት ከተጻፉት ከሌሎቹ ቅዱሳን መጻሕፍት በብዛት በጠቀሰበት ምዕራፍ ውስጥ የክርስቲያን ጉባኤ በክርስቶስ መሠረት ላይ በሕያዋን ድንጋዮች የተገነባ መንፈሳዊ ቤት የሆነበትን መንገድ አስረድቷል። ይህን ያደረገበት ዓላማ ምን ነበር? ጴጥሮስ እንዲህ በማለት መልሱን ይሰጣል:- “ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ፣ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ለራሱ የለያችሁ ሕዝብ ናችሁ።” (1 ጴጥ. 2:4-10፤ ኢሳ. 28:16፤ መዝ. 118:22፤ ኢሳ. 8:14፤ ዘፀ. 19:5, 6፤ ኢሳ. 43:21፤ ሆሴዕ 1:10፤ 2:23) ጴጥሮስ ‘የማይጠፋ፣ የማይበላሽና የማይለወጥ ርስት፣’ ‘የማይጠፋ አክሊል’ እንዲሁም ‘በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የመጠራትን’ የመንግሥቱን ተስፋ እንደሚያገኝ የተናገረለት ‘የንጉሥ ካህናት፣’ የአምላክ ቅዱስ ብሔር የሆነው የካህናት ቡድን ነው። እነሱም ‘ክብሩ በሚገለጥበት ጊዜ ደስታቸው ታላቅ እንዲሆን’ መደሰታቸውን እንዲቀጥሉ ከፍተኛ ማበረታቻ ተሰጥቷቸዋል።—1 ጴጥ. 1:4፤ 5:4, 10፤ 4:13
-