የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋን በመተማመን ተጠባበቁ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 5, 6. (ሀ) ከግብጽ ጋር ኅብረት መፍጠር ለአደጋ የሚዳርግ ስህተት የሆነው ለምንድን ነው? (ለ) አሁን ወደ ግብጽ የሚደረገው ጉዞ ሞኝነት እንደሆነ የሚያሳየው ከዚህ ቀደም የአምላክ ሕዝብ ያደረገው የትኛው ጉዞ ነው?

      5 ኢሳይያስ ወደ ግብጽ የሚደረገው ጉዞ እንዲሁ ድንገተኛ ጉብኝት ይሆን ለሚለው ጥያቄ መልስ መስጠት የፈለገ ይመስል የሚከተለውን ተጨማሪ ዝርዝር መግለጫ ሰጥቷል:- “በደቡብ ስላሉ እንስሶች የተነገረ ሸክም። ተባትና እንስት አንበሳ እፉኝትም ነዘር እባብም በሚወጡባት በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል ብልጥግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ . . . ይሄዳሉ።” (ኢሳይያስ 30:​6) በግልጽ ለመረዳት እንደሚቻለው ጉዞው በሚገባ የታሰበበት ነው። ተጓዦቹ ውድ የሆኑ ሸቀጦች የጫኑባቸውን ግመሎቻቸውንና አህዮቻቸውን አሰልፈው የሚያገሱ አናብስትና መርዘኛ እባቦች በሞሉበት ምድረ በዳ አቋርጠው ወደ ግብጽ ይጓዛሉ። በመጨረሻም ተጓዦቹ ያሰቡት ቦታ ደርሰው የያዙትን ውድ ሀብት ለግብጻውያኑ ያስረክባሉ። በእነርሱ ቤት የግብጽን ከለላ በዋጋ መግዛታቸው ነው። ይሁን እንጂ ይሖዋ እንዲህ ይላል:- “ወደማይጠቅሙአቸው ሕዝብ ይሄዳሉ። የግብጽ እርዳታ ከንቱና ምናምን ነው፤ ስለዚህ ስሙን:- በቤት የሚቀመጥ ረዓብ ብዬ ጠርቼዋለሁ።” (ኢሳይያስ 30:​6, 7) “ረዓብ” የተባለው ‘የባሕር ውስጥ ዘንዶ’ ግብጽን ያመለክታል። (ኢሳይያስ 51:​9, 10) የማትሰጠው ዓይነት የተስፋ ቃል የለም። ነገር ግን አንዱንም አትፈጽምም። ይሁዳ ከእርሷ ጋር ወዳጅነት መፍጠሯ ለጥፋት የሚዳርግ ከባድ ስህተት ነው።

      6 ኢሳይያስ ስለ መልእክተኞቹ ጉዞ ሲገልጽ አድማጮቹ በሙሴ ዘመን የተደረገውን ተመሳሳይ ጉዞ ያስታውሱ ይሆናል። የቀድሞ አባቶቻቸው በዚሁ ‘የሚያስፈራ ምድረ በዳ’ ተጉዘዋል። (ዘዳግም 8:​14-16) ይሁን እንጂ በሙሴ ዘመን እስራኤላውያን በዚህ መንገድ የተጓዙት ከግብጽ ባርነት ነፃ በወጡ ጊዜ ነበር። አሁን ግን መልእክተኞቹ ወደ ግብጽ የሚሄዱት የእነርሱ ተገዥ ለመሆን ነው። እንዴት ያለ ሞኝነት ነው! እኛም መንፈሳዊ ነፃነታችንን በባርነት በመለወጥ ተመሳሳይ የሆነ የቂልነት ውሳኔ እንዳናደርግ እንጠንቀቅ!​—⁠ከ⁠ገላትያ 5:​1 ጋር አወዳድር።

  • ይሖዋን በመተማመን ተጠባበቁ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • [በገጽ 305 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

      በሙሴ ዘመን እስራኤላውያን ከግብጽ ሲያመልጡ በኢሳይያስ ዘመን ደግሞ ይሁዳ እርዳታ ፍለጋ ወደ ግብጽ ሄዳለች

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ