የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋን በመተማመን ተጠባበቁ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 13. የይሁዳ መሪዎች ትምክህታቸውን የጣሉት በምን ነገር ላይ ነበር? እንዲህ ያለውስ ትምክህት ተገቢ ነውን?

      13 ከዚያም ኢሳይያስ እንዲህ በማለት ያብራራል:- “ነገር ግን:- በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም አላችሁ፣ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም:- በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን አላችሁ፣ ስለዚህም የሚያሳድዱአችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።” (ኢሳይያስ 30:​16) የይሁዳ ሰዎች መዳናቸው በይሖዋ ላይ ሳይሆን በፈጣን ፈረሶች የተመካ እንደሆነ አድርገው አስበዋል። (ዘዳግም 17:​16፤ ምሳሌ 21:​31) ይሁን እንጂ ነቢዩ ጠላቶቻቸው ስለሚያገኟቸው ይህ ትምክህታቸው ሕልም ብቻ እንደሆነ በመናገር መልስ ሰጥቷል። ቁጥራቸው የቱንም ያህል ትልቅ ቢሆን የሚያመጣው ለውጥ የለም። “ከአንድ ሰው ዛቻ የተነሣ ሺህ ሰዎች ይሸሻሉ፤ . . . ከአምስት ሰዎች ዛቻ የተነሣ ትሸሻላችሁ።” (ኢሳይያስ 30:​17) የይሁዳ ሠራዊት ሽብር ላይ ስለሚወድቅ እፍኝ በማይሞሉ ጠላቶቻቸው ጩኸት ይሸሻል።a በመጨረሻ “በተራራ ራስ ላይ እንዳለ ምሰሶ፣ በኮረብታም ላይ እንዳለ ምልክት” ሆነው የሚተርፉት ጥቂት ቀሪዎች ብቻ ይሆናሉ። (ኢሳይያስ 30:​17) ኢየሩሳሌም በ607 ከዘአበ ስትጠፋ ልክ በትንቢቱ መሠረት የተረፉት ጥቂት ቀሪዎች ብቻ ናቸው።​—⁠ኤርምያስ 25:​8-11

  • ይሖዋን በመተማመን ተጠባበቁ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • a ይሁዳ የታመነች ሆና ብትገኝ ኖሮ ነገሩ የተገላቢጦሽ ይሆን እንደነበር አትዘንጋ።​—⁠ዘሌዋውያን 26:​7, 8

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ