-
ይሖዋን በመተማመን ተጠባበቁየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
17, 18. በአስቸጋሪ ጊዜያት ሳይቀር ይሖዋ መመሪያ የሚሰጠው እንዴት ነው?
17 ኢሳይያስ ንግግሩን በመቀጠል አድማጮቹን መከራ እንደሚመጣ ያስታውሳቸዋል። ሕዝቡ “የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ” ይቀበላሉ። (ኢሳይያስ 30:20ሀ) በከበባው ወቅት የሚደርስባቸው መከራና ጭቆና የእንጀራና የውኃ ያህል የተለመደ ነገር ይሆናል። ያም ሆኖ ግን ይሖዋ ቅን ልብ ያላቸውን ሰዎች ለመታደግ ዝግጁ ነው። “[“ታላቅ፣” NW] አስተማሪህ እንግዲህ ከአንተ አይሰወርም፤ ዓይኖችህ ግን [“ታላቅ፣” NW] አስተማሪህን ያያሉ፣ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ ብትል ጆሮችህ በኋላህ:- መንገዱ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ የሚለውን ቃል ይሰማሉ።”—ኢሳይያስ 30:20ለ, 21b
18 ይሖዋ “ታላቅ አስተማሪ” ነው። በአስተማሪነቱ አቻ የለውም። ይሁንና ሰዎች እርሱን ‘ሊያዩትና’ ‘ሊሰሙት’ የሚችሉት እንዴት ነው? ይሖዋ ቃላቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተመዘገበው ነቢያቱ አማካኝነት ራሱን ይገልጣል። (አሞጽ 3:6, 7) ዛሬ የታመኑ አምላኪዎች መጽሐፍ ቅዱስን ሲያነብቡ የአምላክ አባታዊ ድምፅ የሚሄዱበትን መንገድ የሚነግራቸውና በዚያ መንገድ መመላለስ ይችሉ ዘንድ ጎዳናቸውን እንዲያስተካክሉ አጥብቆ የሚያሳስባቸው ያህል ነው። ይሖዋ በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾችና “ታማኝና ልባም ባሪያ” በሚያዘጋጃቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች አማካኝነት ሲናገር እያንዳንዱ ክርስቲያን በጥንቃቄ ማዳመጥ ይኖርበታል። (ማቴዎስ 24:45-47) እያንዳንዱ ሰው ‘ሕይወቱ ነውና’ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ መትጋት አለበት።—ዘዳግም 32:46, 47፤ ኢሳይያስ 48:17
-
-
ይሖዋን በመተማመን ተጠባበቁየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
b መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይሖዋ “ታላቅ አስተማሪ” ተብሎ የተጠራበት ቦታ ይህ ብቻ ነው።
-