የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ በደስታ እንድንጸና የሚረዳን እንዴት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022 | ኅዳር
    • ይሖዋ ይመራናል

      8. በኢሳይያስ 30:20, 21 ላይ የሚገኘው ትንቢት በጥንት ዘመን የተፈጸመው እንዴት ነው?

      8 ኢሳይያስ 30:20, 21⁠ን አንብብ። የባቢሎን ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ለአንድ ዓመት ተኩል ከብቦ በቆየበት ጊዜ ሕዝቡ ጭንቀት የምግብና የውኃ ያህል የዕለት ተዕለት ጉዳይ ሆኖባቸው ነበር። ሆኖም በቁጥር 20 እና 21 ላይ ይሖዋ፣ አይሁዳውያኑ ንስሐ ከገቡና አካሄዳቸውን ካስተካከሉ እንደሚያድናቸው ቃል ገብቶላቸዋል። ኢሳይያስ ‘ታላቅ አስተማሪ’ የሆነው ይሖዋ፣ ሕዝቡ እሱን ተቀባይነት ባለው መንገድ ማምለክ የሚችሉት እንዴት እንደሆነ እንደሚያስተምራቸው ነግሯቸዋል። አይሁዳውያን ከግዞት ነፃ ሲወጡ ይህ ትንቢት ተፈጽሟል። ይሖዋ ታላቅ አስተማሪ ሆኖላቸዋል፤ በእሱ አመራር ሥር ሕዝቡ ንጹሕ አምልኮን መልሰው ማቋቋም ችለዋል። በዛሬው ጊዜም ይሖዋ ታላቅ አስተማሪ ስለሆነልን አመስጋኞች ነን።

  • ይሖዋ በደስታ እንድንጸና የሚረዳን እንዴት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022 | ኅዳር
    • 10. ‘ከኋላችን ድምፅ’ የምንሰማው እንዴት ነው?

      10 ኢሳይያስ፣ ይሖዋ እኛን ለማስተማር የሚጠቀምበትን ሁለተኛ መንገድ ሲገልጽ “ጆሮህ ከኋላህ . . . ድምፅ ይሰማል” ብሏል። ኢሳይያስ እዚህ ላይ ይሖዋን ከተማሪዎቹ ኋላ ኋላ እየሄደ አቅጣጫ እንደሚጠቁም ንቁ አስተማሪ አድርጎ ገልጾታል። በዛሬው ጊዜ የአምላክን ድምፅ ከኋላችን እንሰማለን። እንዴት? አምላክ በመንፈስ መሪነት መጽሐፍ ቅዱስን ያስጻፈው ከረጅም ጊዜ በፊት ነው፤ ከኋላችን ሊባል ይችላል። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ የአምላክን ድምፅ ከኋላችን የምንሰማ ያህል ነው።—ኢሳ. 51:4

      11. በደስታ ለመጽናት የትኞቹን እርምጃዎች መውሰድ ይኖርብናል? ለምንስ?

      11 ይሖዋ በድርጅቱና በቃሉ አማካኝነት ከሚሰጠው አመራር የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው? ኢሳይያስ ሁለት ነገሮችን እንደጠቀሰ ልብ በሉ። አንደኛ፣ “መንገዱ ይህ ነው።” ሁለተኛ፣ “በእሱ ሂድ።” (ኢሳ. 30:21) ስለዚህ ‘መንገዱን’ ማወቅ ብቻ በቂ አይደለም። ‘በእሱ ልንሄድም’ ይገባል። በይሖዋ ቃልና ድርጅቱ በሚሰጠው ማብራሪያ አማካኝነት ይሖዋ ምን እንደሚጠብቅብን እንማራለን። የተማርነውን እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደምንችልም እንማራለን። ለይሖዋ በምናቀርበው አገልግሎት በደስታ ለመጽናት ከፈለግን ሁለቱንም እርምጃዎች መውሰድ ይጠበቅብናል። ይሖዋ እንደሚባርከን እርግጠኞች መሆን የምንችለው ይህን ካደረግን ብቻ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ