የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋን በመተማመን ተጠባበቁ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 21. የሚመጣው በረከት ምን ያህል የተሟላ እንደሆነ ግለጽ።

      21 “በረጅሙ ተራራ ሁሉ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይሆናሉ።” (ኢሳይያስ 30:​25)c ኢሳይያስ የይሖዋ በረከት ምን ያህል የተሟላ እንደሆነ ጎላ አድርጎ ለማሳየት ተስማሚ መግለጫ ተጠቅሟል። የውኃ እጥረት አይኖርም። ውድ ነገር የሆነው ውኃ በረባዳማ መሬቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በየተራራው ሁሉ ‘በረጅሙ ተራራና ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ’ ላይ ሳይቀር ይፈስሳል። አዎን፣ ረሃብ የተረሳ ነገር ይሆናል። (መዝሙር 72:​16) ከዚያም ነቢዩ ትኩረቱን ከተራራም በላይ ከፍ ወዳሉ ነገሮች ያዞራል። “እግዚአብሔርም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፣ መቅሠፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፣ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፣ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።” (ኢሳይያስ 30:​26) ለዚህ ድንቅ ትንቢት ይህ እንዴት ያለ አስደሳች መደምደሚያ ነው! የአምላክ ክብር በሙሉ ኃይሉ ደማቅ ሆኖ ይበራል። ለታመኑት የአምላክ አገልጋዮች የተዘጋጁት በረከቶች ከዚያ ቀደም ከታየው ሁሉ በበለጠ መጠን ሰባት እጥፍ ሆነው ይፈስሳሉ።

  • ይሖዋን በመተማመን ተጠባበቁ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • c የ⁠ኢሳይያስ 30:​25 የቀረው ክፍል “በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ” ይላል። የዚህ ትንቢት የመጀመሪያ ፍጻሜ የባቢሎንን ውድቀት የሚያመለክት ሊሆን ይችላል። ይህ ደግሞ እስራኤላውያን በ⁠ኢሳይያስ 30:​18-26 ላይ የተጠቀሱትን በረከቶች እንዲያገኙ በር የከፈተ እርምጃ ነው። (አንቀጽ 19ን ተመልከት።) እነዚህ በረከቶች በአዲሱ ዓለም ውስጥ የላቀ ፍጻሜያቸውን እንዲያገኙ በር የሚከፍተውን የአርማጌዶን የጥፋት እርምጃም ሊያመለክት ይችላል።

  • ይሖዋን በመተማመን ተጠባበቁ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • [በገጽ 311 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

      “ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይሆናሉ”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ