የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ንጉሡና መሳፍንቱ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 5-7. በትንቢት የተነገረላቸው ‘መሳፍንት’ በአምላክ መንጋ መካከል ምን ሚና ይጫወታሉ?

      5 ይሁን እንጂ ይህ በጥላቻ የተሞላ ዓለም እስካለ ድረስ የእጅግ ብዙ ሰዎች አባላት ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል። በአመዛኙ ይህን ጥበቃ የሚያገኙት ‘በፍትሕ ከሚያስተዳድሩት’ “መሳፍንት” ነው። እንዴት ድንቅ ዝግጅት ነው! ‘መሳፍንቱ’ በኢሳይያስ ትንቢት ውስጥ በሚከተሉት አስደሳች ቃላት ተገልጸዋል:- “ሰውም ከነፋስ እንደ መሸሸጊያ ከዐውሎ ነፋስም እንደ መጠጊያ፣ በጥም ቦታም እንደ ወንዝ ፈሳሽ፣ በበረሀም አገር እንደ ትልቅ ድንጋይ ጥላ ይሆናል።”​—⁠ኢሳይያስ 32:​2

      6 በዓለም ዙሪያ ጭንቀት በነገሠበት በአሁኑ ዘመን የይሖዋን በጎች በመንከባከብና ከይሖዋ የጽድቅ መሠረታዊ ሥርዓት ጋር በሚስማማ መንገድ ፍትሕን በማስፈጸም ‘ለመንጋው የሚጠነቀቁ’ “መሳፍንት” ማለትም ሽማግሌዎች ያስፈልጋሉ። (ሥራ 20:​28) እንደነዚህ ያሉት “መሳፍንት” በ⁠1 ጢሞቴዎስ 3:​2-7 እና በ⁠ቲቶ 1:​6-9 ላይ የተዘረዘረውን ብቃት ማሟላት ይኖርባቸዋል።

      7 ኢየሱስ አስጨናቂ ስለሆነው ‘የነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ’ በገለጸበት ታላቅ ትንቢት ውስጥ “አትሸበሩ” ሲል ተናግሯል። (ማቴዎስ 24:​3-8 NW ) የኢየሱስ ተከታዮች ዛሬ ባለው አደገኛ የዓለም ሁኔታ የማይሸበሩት ለምንድን ነው? አንደኛው ምክንያት ከቅቡዓንም ሆነ ‘ከሌሎች በጎች’ ወገን የሆኑ “መሳፍንት” በታማኝነት መንጋውን በመጠበቅ ላይ ስለሆኑ ነው። (ዮሐንስ 10:​16) የጎሳ ጦርነትንና የጅምላ ጭፍጨፋን በመሳሰሉ አስፈሪ ወቅቶች ሳይቀር ያላንዳች ፍርሃት ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን ይንከባከባሉ። የአምላክ ቃል በሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን የሚያንጽ እውነት በመጠቀም በመንፈሳዊ በተራቆተው በዚህ ዓለም ውስጥ ያዘኑትን ሰዎች መንፈስ ለማደስ ይጥራሉ።

      8. ይሖዋ የሌሎች በጎች ክፍል የሆኑትን “መሳፍንት” እያሰለጠናቸውና እየተጠቀመባቸው ያለው እንዴት ነው?

      8 ባለፉት 50 ዓመታት ‘መሳፍንቱ’ ያላቸው ቦታ ይበልጥ ጉልህ ሆኗል። ‘የሌሎች በጎች’ ክፍል የሆኑት “መሳፍንት” ‘የአለቃው’ ቡድን ሆነው ሥልጠና እያገኙ ሲሆን ከታላቁ መከራ በኋላ ከመካከላቸው ብቃት ያላቸው በአዲሱ ምድር ውስጥ በአስተዳደር ሥራ ለማገልገል ዝግጁ ይሆናሉ። (ሕዝቅኤል 44:​2, 3፤ 2 ጴጥሮስ 3:​13) በመንግሥቱ አገልግሎት ቀዳሚ ሆነው እየሠሩ መንፈሳዊ መመሪያና ማነቃቂያ በመስጠት ከአምልኮ ጋር በተያያዘ ለመንጋው “እንደ ትልቅ ድንጋይ ጥላ” እረፍትን የሚሰጡ መሆናቸውን እያረጋገጡ ነው።b

      9. ዛሬ ‘መሳፍንት’ እንደሚያስፈልጉ የሚያሳዩት ሁኔታዎች የትኞቹ ናቸው?

      9 አደገኛ በሆኑት በእነዚህ የሰይጣን ክፉ ዓለም የመጨረሻ ቀናት ራሳቸውን ለአምላክ የወሰኑ ክርስቲያኖች እንዲህ ያለው ጥበቃ በእጅጉ ያስፈልጋቸዋል። (2 ጢሞቴዎስ 3:​1-5, 13) ዛሬ የሐሰት መሠረተ ትምህርቶችና የተጣመመ ፕሮፓጋንዳ እንደ ኃይለኛ ነፋስ የሚነፍሱበት ጊዜ ነው። በብሔራት መካከልም ሆነ በየአገራቱ እርስ በርስ የሚደረገው ጦርነት እንዲሁም በይሖዋ አምላክ የታመኑ አምላኪዎች ላይ በቀጥታ የሚሰነዘረው ጥቃት እንደ ዐውሎ ነፋስ እያስገመገመ ነው። ክርስቲያኖች በመንፈሳዊ ድርቅ በተመታው ዓለም ውስጥ መንፈሳዊ ጥማቸውን ለማርካት ንጹህ የሆነውና ያልተበረዘው የእውነት የወንዝ ፈሳሽ ያስፈልጋቸዋል። የሚያስደስተው ደግሞ ይሖዋ በመግዛት ላይ ያለው ንጉሡ በዚህ የችግር ወቅት በቅቡዓን ወንድሞቹና በተባባሪዎቻቸው የሌሎች በጎች “መሳፍንት” በመጠቀም ለተጨነቁትና ተስፋ ለቆረጡት ሰዎች አስፈላጊውን ማበረታቻ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል። በዚህ መንገድ ይሖዋ ጽድቅና ፍትሕ እንዲሰፍን ያደርጋል።

  • ንጉሡና መሳፍንቱ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • [በገጽ 333 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

      እያንዳንዱ ‘መስፍን ’ ከነፋስ እንደ መሸሸጊያ፣ ከዝናብ እንደ መጠለያ፣ በበረሃ እንዳለ ውኃ እንዲሁም ከፀሐይ እንደሚያስጥል ጥላ ነው

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ