የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘በዚያም የሚቀመጥ ታምሜአለሁ አይልም’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 5 በዚያ አስፈሪ ወቅት የታመኑ የይሖዋ አምላኪዎች ለእርዳታ ወደ ይሖዋ ዞር ማለት ነበረባቸው። በመሆኑም ኢሳይያስ እንዲህ ሲል ጸልዮአል:- “አቤቱ፣ ማረን፤ አንተን ተማምነናል፤ ጥዋት ጥዋት [የብርታትና የመደገፊያ ] ክንድ በመከራም ጊዜ ማዳን ሁነን። ከፍጅት ድምፅ ወገኖች ሸሹ፣ በመነሣትህም አሕዛብ ተበተኑ።” (ኢሳይያስ 33:​2, 3) ኢሳይያስ ይሖዋ ከዚያ ቀደም ብዙ ጊዜ እንዳደረገው ሁሉ አሁንም ሕዝቡን እንዲታደግ መጸለዩ ተገቢ ነበር። (መዝሙር 44:​3፤ 68:​1) ኢሳይያስ ይህን ጸሎት ካቀረበ በኋላ አፍታም ሳይቆይ ይሖዋ ለዚህ ጸሎት ስለሚሰጠው ምላሽ ትንቢት ተናግሯል!

  • ‘በዚያም የሚቀመጥ ታምሜአለሁ አይልም’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • የዘመናችን አሦር

      7.(ሀ) በመንፈሳዊ የታመመችው እስራኤል በዛሬው ጊዜ ከማን ጋር ልትነጻጸር ትችላለች? (ለ) ሕዝበ ክርስትናን ለማጥፋት ለይሖዋ እንደ “በትር” ሆኖ የሚያገለግለው ማን ነው?

      7 የኢሳይያስ ትንቢት ለዘመናችን የሚሠራው እንዴት ነው? በመንፈሳዊ ሕመም ተይዞ የነበረው የእስራኤል ሕዝብ ከሃዲ ከሆነችው ሕዝበ ክርስትና ጋር ሊመሳሰል ይችላል። ይሖዋ እስራኤልን ለመቅጣት አሦርን እንደ “በትር” እንደተጠቀመበት ሁሉ ሕዝበ ክርስትናንም ሆነ የቀረውን የዓለም የሐሰት ሃይማኖት ግዛት ማለትም ‘ታላቂቱ ባቢሎንን’ ለመቅጣት ‘በበትር’ ይጠቀማል። (ኢሳይያስ 10:​5፤ ራእይ 18:​2-8) ይሖዋ እንደ “በትር” የሚጠቀመው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል አገራትን ይሆናል። ይህ ድርጅት በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ሰባት ራስና አሥር ቀንድ ባለው ቀይ አውሬ ተመስሏል።​—⁠ራእይ 17:​3, 15-17

      8. (ሀ) ዛሬ ያለው የሰናክሬም አምሳያ ማን ነው? (ለ) የዘመናችን ሰናክሬም ልቡን አደንድኖ የሚነሣው ማንን ለማጥቃት ነው? ውጤቱስ ምን ይሆናል?

      8 የዘመናችን አሦር በሐሰት ሃይማኖት ግዛት ውስጥ ሲፈነጭ የሚያቆመው ያለ አይመስልም። ሰይጣን ዲያብሎስ የሰናክሬም ዓይነት ዝንባሌ በመያዝ ጥቃት ለመሰንዘር ልቡን አደንድኖ ይነሳል። ጥቃቱን የሚሰነዝረው ግን ቅጣት በሚገባቸው ከሃዲ ድርጅቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በእውነተኛ ክርስቲያኖች ላይ ጭምር ነው። ታላቂቱ ባቢሎንን ከሚጨምረው የሰይጣን ዓለም የወጡ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከይሖዋ የተቀቡ መንፈሳዊ ልጆች ቀሪዎች ጋር በመተባበር ከይሖዋ መንግሥት ጎን ለመቆም መርጠዋል። “የዚህ ዓለም አምላክ” የሆነው ሰይጣን እውነተኛ ክርስቲያኖች ለእርሱ ስለማያጎበድዱ ተቆጥቶ መጠነ ሰፊ ጥቃት ይሰነዝርባቸዋል። (2 ቆሮንቶስ 4:​4፤ ሕዝቅኤል 38:​10-16) ይህ ጥቃት እጅግ አስፈሪ እንደሚሆን ምንም ባያጠራጥርም የይሖዋ ሕዝብ በፍርሃት የሚርበተበትበት አንዳችም ምክንያት የለም። (ኢሳይያስ 10:​24, 25) አምላክ ‘በመከራ ጊዜ እንደሚያድናቸው’ ማረጋገጫ ሰጥቷቸዋል። በሰይጣንና በጭፍሮቹ ላይ ጥፋት በማምጣት እጁን ጣልቃ ያስገባል። (ሕዝቅኤል 38:​18-23) በጥንት ዘመን እንደሆነው ሁሉ የአምላክን ሕዝብ ለመበዝበዝ የሚሞክሩ ወገኖች ራሳቸው ይበዘበዛሉ! (ከ⁠ምሳሌ 13:​22ለ ጋር አወዳድር።) የይሖዋ ስም ይቀደሳል። በሕይወት የሚተርፉትም ሰዎች ‘ጥበብንና እውቀትን እንዲሁም ይሖዋን መፍራትን ’ በመፈለጋቸው ይባረካሉ።​—⁠ኢሳይያስ 33:​5, 6ን አንብብ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ