የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘በዚያም የሚቀመጥ ታምሜአለሁ አይልም’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • ፈውስ

      20. የአምላክ ሕዝብ ምን ዓይነት ፈውስ ያገኛል? መቼ?

      20 ይህኛው የኢሳይያስ ትንቢት ክፍል የሚደመደመው ልብን ደስ በሚያሰኝ ተስፋ ነው:- “በዚያም የሚቀመጥ:- ታምሜአለሁ አይልም፣ በእርስዋም ለሚቀመጡ ሰዎች በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋል።” (ኢሳይያስ 33:​24) ኢሳይያስ እዚህ ላይ እየተናገረለት ያለው ሕመም ከኃጢአት ወይም ‘ከበደል’ ጋር የተያያዘ በመሆኑ በዋነኝነት የሚያመለክተው መንፈሳዊ ሕመምን ነው። በእነዚህ ቃላት የመጀመሪያ ደረጃ ፍጻሜ መሠረት ይሖዋ ብሔሩ ከባቢሎን ምርኮ ነፃ ከወጣ በኋላ ከመንፈሳዊ ሕመሙ እንደሚፈወስ ቃል ገብቷል። (ኢሳይያስ 35:​5, 6፤ ኤርምያስ 33:​6፤ ከ⁠መዝሙር 103:​1-5 ጋር አወዳድር።) ከምርኮ ተመላሾቹ አይሁዳውያን የቀድሞ ኃጢአታቸው ይቅር ስለተባለላቸው እውነተኛውን አምልኮ በኢየሩሳሌም መልሰው ያቋቁማሉ።

      21. ዛሬ ያሉ የይሖዋ አምላኪዎች መንፈሳዊ ፈውስ የሚያገኙት በምን መንገዶች ነው?

      21 ይሁንና የኢሳይያስ ትንቢት በዘመናችንም ተፈጻሚነት ይኖረዋል። ዛሬ ያለው የይሖዋ ሕዝብም መንፈሳዊ ፈውስ አግኝቷል። ነፍስ አትሞትም፣ ሥላሴ እና የሲኦል እሳት የሚሉትን ከመሳሰሉት የሐሰት ትምህርቶች ነፃ ወጥተዋል። ከሥነ ምግባር ብልግና እንዲላቀቁና ጥሩ ውሳኔዎችን እንዲያደርጉ የሚረዳቸውን የግብረገብ መመሪያ ያገኛሉ። እንዲሁም ለኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት ምሥጋና ይግባውና በአምላክ ፊት ንጹሕ አቋም ኖሯቸው ንጹህ ሕሊና ለማግኘት በቅተዋል። (ቆላስይስ 1:​13, 14፤ 1 ጴጥሮስ 2:​24፤ 1 ዮሐንስ 4:​10) ይህ መንፈሳዊ ፈውስ አካላዊ ጥቅምም አለው። ለምሳሌ ያህል ክርስቲያኖች ከፆታ ብልግናና ከትንባሆ ውጤቶች በመራቃቸው በፆታ ግንኙነት ከሚተላለፉ በሽታዎችና ከአንዳንድ የካንሰር ዓይነቶች ተጠብቀዋል።​—⁠1 ቆሮንቶስ 6:​18፤ 2 ቆሮንቶስ 7:​1

      22, 23. (ሀ) ኢሳይያስ 33:​24 ወደፊት ምን ታላቅ ፍጻሜ ይኖረዋል? (ለ) ዛሬ ያሉ እውነተኛ አምላኪዎች ቁርጥ ውሳኔ ምንድን ነው?

      22 ከዚህም በተጨማሪ በ⁠ኢሳይያስ 33:​24 ላይ የሚገኙት ቃላት ከአርማጌዶን በኋላ በሚኖረው የአምላክ አዲስ ዓለም ውስጥም ታላቅ ፍጻሜ ይኖራቸዋል። የሰው ልጅ በመሲሐዊው መንግሥት አገዛዝ ሥር ከሚያገኘው መንፈሳዊ ፈውስ በተጨማሪ ታላቅ አካላዊ ፈውስ ያገኛል። (ራእይ 21:​3, 4) የሰይጣን ክፉ የነገሮች ሥርዓት ከጠፋ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ኢየሱስ ምድር ሳለ ያከናወናቸውን ዓይነት ተዓምራት በምድር ዙሪያ እንደሚከናወኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ዕውራን ያያሉ፣ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፣ አንካሳውም በእግሮቹ ይራመዳል! (ኢሳይያስ 35:​5, 6) ይህም ከታላቁ መከራ በሕይወት የተረፉት ሰዎች በሙሉ ምድርን ወደ ገነትነት በመለወጡ ታላቅ ሥራ መካፈል የሚችሉበትን አጋጣሚ ይከፍታል።

      23 ከጊዜ በኋላ ትንሣኤ ሲጀምር ደግሞ ከሞት የሚነሱት ሰዎች ጥሩ ጤና ኖሯቸው እንደሚነሱ ምን አያጠራጥርም። ይሁን እንጂ ቤዛው ይበልጥ ጥቅም ላይ እየዋለ ሲሄድ የሰውን ልጅ ፍጽምና ደረጃ ላይ እስከማድረስ ድረስ ተጨማሪ አካላዊ ጥቅሞች ይኖሩታል። ጻድቃን ‘በሕይወት ኖረዋል’ ሊባል የሚችለው በዚህ ጊዜ ነው። (ራእይ 20:​5, 6) በዚያ ጊዜ በመንፈሳዊም ሆነ በአካላዊ ሁኔታ ‘ታምሜአለሁ የሚል አይኖርም።’ እንዴት አስደሳች ተስፋ ነው! ዛሬ ያሉ እውነተኛ አምላኪዎች በሙሉ ቁርጥ ውሳኔያቸው የዚህን ትንቢት ፍጻሜ ከሚያጣጥሙት ሰዎች መካከል መገኘት መሆን ይኖርበታል!

  • ‘በዚያም የሚቀመጥ ታምሜአለሁ አይልም’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • [በገጽ 353 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

      ለቤዛዊ መሥዋዕቱ ምስጋና ይግባውና የይሖዋ ሕዝብ በእርሱ ፊት ንጹህ አቋም ለማግኘት በቅቷል

      [በገጽ 354 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

      በአዲሱ ዓለም ውስጥ ታላቅ አካላዊ ፈውስ ይከናወናል

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ