የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ በብሔራት ላይ ቁጣውን ያፈስሳል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 7. “ሰማያት” የተባሉት ምንድን ናቸው? ‘የሰማይ ሠራዊትስ?’

      7 ኢሳይያስ ተጨማሪ ሕያው የሆነ ሥዕላዊ መግለጫ ሲሰጥ እንዲህ ይላል:- “የሰማይም ሠራዊት ሁሉ ይበሰብሳሉ፣ ሰማያትም እንደ መጽሐፍ ጥቅልል ይጠቀለላሉ፣ ከወይንና ከበለስም ቅጠል እንደሚረግፍ [“እንደጠወለገ የወይን ቅጠልና እንደሟሸሸ የበለስ ፍሬ፣” NW ] ሠራዊታቸው ሁሉ ይረግፋል።” (ኢሳይያስ 34:​4) ‘የሰማይ ሠራዊት’ የሚለው መግለጫ ቃል በቃል ከዋክብትንና ፕላኔቶችን የሚያመለክት አይደለም። ኢሳይያስ 34 ቁጥር 5 እና 6 ላይ በእነዚያ “ሰማያት” ውስጥ በደም የሚነከር የቅጣት ሰይፍ እንዳለ ተገልጿል። በመሆኑም ይህ በሰብዓዊው ዓለም ያለን ነገር የሚያመለክት ምሳሌ መሆን ይኖርበታል። (1 ቆሮንቶስ 15:​50) የሰው ልጅ መስተዳድሮች ባላቸው የበላይ ሥልጣን ከፍ ብለው ስለሚታዩ በምድራዊው ሰብዓዊ ኅብረተሰብ ላይ የሚገዙ ሰማያት እንደሆኑ ተደርገው ተገልጸዋል። (ሮሜ 13:​1-4) በመሆኑም ‘የሰማይ ሠራዊት’ የተባሉት የእነዚህ የሰው ዘር መንግሥታት ሠራዊቶች በጠቅላላ ናቸው።

      8. ምሳሌያዊዎቹ ሰማያት “እንደ መጽሐፍ ጥቅልል” የሚሆኑት እንዴት ነው? ‘ሠራዊቶቻቸውስ’ ምን ይሆናሉ?

      8 ይህ “ሠራዊት” ‘ይበሰብሳል’ ማለትም እንደ አንድ የሚበላሽ ነገር ይሻግታል። (መዝሙር 102:​26፤ ኢሳይያስ 51:​6) ከበላያችን ያለውን ሰማይ ቀና ብለን ስናየው በጥቅልል መልክ እንደሚዘጋጁትና በአብዛኛው ከውስጥ በኩል ብቻ እንደሚጻፍባቸው የጥንት የመጻሕፍት ጥቅልሎች መሀሉ ሰርጎድ ብሎ ይታየናል። በጥቅልሉ ውስጠኛ ክፍል ላይ የተጻፈው ነገር ከአንባቢው ዓይን ሲያልፍ ያለቀው ገጽ ይጠቀለላል። በተመሳሳይም ‘ሰማያት እንደ መጽሐፍ ጥቅልል ተጠቅልለው ሲያልፉ’ የሰብዓዊ መስተዳድሮች ፍጻሜ ይሆናል። አርማጌዶን የታሪካቸው የመጨረሻ ገጽ ስለሚሆን ሕልውናቸው እዚያ ላይ ያከትማል። አስፈሪ መስለው የሚታዩት ‘ሠራዊቶቻቸው’ ከወይን ተክል ላይ እንደሚረግፍ ቅጠል ወይም ከበለስ ዛፍ ላይ እንደሚወድቅ ‘የሟሸሸ በለስ’ ይወድቃሉ። ጊዜ ያለፈባቸው ይሆናሉ።​—⁠ከ⁠ራእይ 6:​12-14 ጋር አወዳድር።

  • ይሖዋ በብሔራት ላይ ቁጣውን ያፈስሳል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • [በገጽ 360 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

      “ሰማያትም እንደ መጽሐፍ ጥቅልል ይጠቀለላሉ”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ