-
ይሖዋ በብሔራት ላይ ቁጣውን ያፈስሳልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
የበቀል ቀን
9. (ሀ) የኤዶምያስ ዝርያ ከየት የመጣ ነው? በእስራኤልና በኤዶምያስ መካከል የነበረው ግንኙነትስ ምን ይመስል ነበር? (ለ) ይሖዋ ኤዶምያስን በተመለከተ የተናገረው ነገር ምንድን ነው?
9 አሁን ደግሞ ትንቢቱ በኢሳይያስ ዘመን የነበረችውን አንዲት ብሔር ማለትም ኤዶምያስን ነጥሎ ይጠቅሳል። ኤዶማውያን ብኩርናውን መንትያው ለሆነው ወንድሙ ለያዕቆብ በእንጀራና በምስር ወጥ የሸጠው የኤሳው (የኤዶም) ዝርያዎች ናቸው። (ዘፍጥረት 25:24-34) ያዕቆብ የብኩርናውን ቦታ ስለወሰደበት ኤሳው ለወንድሙ ከፍተኛ ጥላቻ አድሮበት ነበር። በኋላም የኤዶምያስና የእስራኤል ብሔራት የሁለት መንትያ ወንድማማቾች ልጆች ቢሆኑም እንደ ጠላት ሲተያዩ ኖረዋል። ኤዶምያስ ለአምላክ ሕዝብ ላሳየችው ለዚህ ጥላቻዋ የይሖዋን ቁጣ አትርፋለች። በመሆኑም ይሖዋ እንዲህ ይላታል:- “ሰይፌ በሰማይ ሆና እስክትረካ ድረስ ጠጥታለች፤ እነሆ፣ በኤዶምያስና በረገምሁት ሕዝብ ላይ ለፍርድ ትወርዳለች። እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፣ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፣ በስብም፣ በበግ ጠቦትና በፍየል ደምም፣ በአውራም በግ ኩላሊት ስብ ወፍራለች።”—ኢሳይያስ 34:5, 6
10. (ሀ) ይሖዋ ‘በሰማያት ውስጥ’ ሰይፉን ሲመዝዝ አሽቀንጥሮ የሚጥለው ማንን ይሆናል? (ለ) ይሁዳ በባቢሎን ጥቃት ሲሰነዘርባት ኤዶምያስ ያሳየችው ዝንባሌ ምን ነበር?
10 ኤዶምያስ የምትገኘው ከፍ ባለ ተራራማ ቦታ ላይ ነው። (ኤርምያስ 49:16፤ አብድዩ 8, 9, 19, 21) ያም ሆነ ይህ ይሖዋ የፍርድ ሰይፉን ‘በሰማያቱ ውስጥ’ መዝዞ የኤዶምያስን መሪዎች ከፍ ካለው ቦታቸው ሲያሽቀነጥራቸው እነዚህ ተፈጥሮአዊ መከላከያዎች የሚፈይዱት ነገር አይኖርም። ኤዶምያስ ከፍተኛ ወታደራዊ ኃይል ያላትና የጦር ሠራዊቷም ከፍ ባሉት ተራሮች ሰንሰለት ላይ እየተሽሎከለከ የሚጠብቃት ምድር ነች። ይሁን እንጂ ኃያል የሆነችው ኤዶምያስ ይሁዳ በባቢሎን ሠራዊት በተጠቃች ጊዜ እርሷን ለመርዳት ያደረገችው ነገር አልነበረም። ከዚህ ይልቅ የይሁዳ መንግሥት በመገልበጡ ተደስታ ወራሪውን ኃይል አይዞህ ትል ነበር። (መዝሙር 137:7) እንዲያውም ኤዶምያስ ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሸሽተው የሚያመልጡትን አይሁዳውያን አሳድዳ እየያዘች ለባቢሎናውያን አሳልፋ ትሰጥ ነበር። (አብድዩ 11-14) የኤዶማውያኑ እቅድ እስራኤላውያን ትተውት የሚሄዱትን አገር መውሰድ ነበር። በይሖዋም ላይ በጉራ ተናግረዋል።—ሕዝቅኤል 35:10-15
-
-
ይሖዋ በብሔራት ላይ ቁጣውን ያፈስሳልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
12. (ሀ) ይሖዋ ኤዶምያስን ለመቅጣት መሣሪያ አድርጎ የሚጠቀመው ማንን ነው? (ለ) ነቢዩ አብድዩ ኤዶምያስን በተመለከተ ምን ትንቢት ተናግሯል?
12 አምላክ ጽዮን በምትባለው ምድራዊ ድርጅቱ ላይ ስትፈጽመው ለቆየችው የተንኮል ድርጊት ኤዶምያስን ሊቀጣት ዓላማ አለው። ትንቢቱ እንዲህ ይላል:- “የእግዚአብሔር የበቀሉ ቀን፣ ስለ ጽዮንም ክርክር የብድራት ዓመት ነው።” (ኢሳይያስ 34:8) ኢየሩሳሌም በ607 ከዘአበ ከጠፋች በኋላ ብዙም ሳይቆይ ይሖዋ የባቢሎኑን ንጉሥ ናቡከደነፆርን በመጠቀም በኤዶማውያን ላይ የጽድቅ የበቀል እርምጃ መውሰድ ጀምሯል። (ኤርምያስ 25:15-17, 21) የባቢሎን ሠራዊት በኤዶምያስ ላይ ሲዘምት ኤዶማውያንን የሚያስጥላቸው አይኖርም! በዚያች ተራራማ አገር ላይ የመጣ “የብድራት ዓመት ነው።” ይሖዋ በነቢዩ አብድዩ አማካኝነት እንዲህ ሲል አስቀድሞ ተናግሯል:- “በወንድምህ በያዕቆብ ላይ ስለ ተደረገ ግፍ እፍረት ይከድንሃል፣ ለዘላለምም ትጠፋለህ። . . . አንተ እንዳደረግኸው እንዲሁ ይደረግብሃል፣ ፍዳህም በራስህ ላይ ይመለሳል።”—አብድዩ 10, 15፤ ሕዝቅኤል 25:12-14
የሕዝበ ክርስትና የጨለመ ተስፋ
13. ዛሬ ከኤዶምያስ ጋር የምትመሳሰለው ማን ናት? ለምንስ?
13 በዛሬው ጊዜም እንደ ኤዶምያስ ዓይነት ታሪክ ያስመዘገበ ድርጅት አለ። የትኛው ድርጅት ነው? በዚህ በዘመናችን የይሖዋን አገልጋዮች በመስደብና በማሳደድ ግንባር ቀደም የሆነው ማን ነው ብለን እንጠይቅ። በቀሳውስቷ አማካኝነት ይህንን ስታደርግ የኖረችው ሕዝበ ክርስትና አይደለችምን? አዎን! ሕዝበ ክርስትና በዚህ ዓለም ጉዳዮች እንደ ተራራ ከፍ ያለ ቦታ ይዛለች። በሰው ልጅ የነገሮች ሥርዓት ውስጥ ከፍ ያለ ቦታ አለኝ ትላለች። እንዲሁም ሃይማኖቶቿ በታላቂቱ ባቢሎን ውስጥ ጉልህ ስፍራ አላቸው። ይሁን እንጂ ይሖዋ ዘመናዊቷ ኤዶምያስ በሕዝቡ ማለትም በምሥክሮቹ ላይ ስለፈጸመችው አሰቃቂ ተግባር “የብድራት ዓመት” ቀጥሮባታል።
-