የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ በብሔራት ላይ ቁጣውን ያፈስሳል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 16, 17. ኤዶምያስ ምን ትሆናለች? በእንዲህ ዓይነት ሁኔታስ የምትቀጥለው እስከ መቼ ነው?

      16 የኢሳይያስ ትንቢት የኤዶምያስ ሰብዓዊ ኅብረተሰብ በአራዊት እንደሚተካ በመናገር የሚሰጠውን መግለጫ ይቀጥላል። ይህም አባባል ባድማ እንደምትሆን የሚያመለክት ነው:- “ከትውልድ እስከ ትውልድም ድረስ ባድማ ሆና ትኖራለች፤ ለዘላለም ዓለም ማንም አያልፍባትም። ጭልፊትና ጃርት ግን ይወርሱአታል፤ ጉጉትና ቁራም ይኖሩባታል፤ በላይዋም የመፍረስ ገመድና የባዶነት ቱንቢ ይዘረጋባታል። መሳፍንቶችዋን ወደ መንግሥት ይጠራሉ፣ ነገር ግን ማንም አይገኝባትም፤ አለቆችዋም ሁሉ ምናምኖች ይሆናሉ። በአዳራሾችዋም እሾህ በቅጥሮችዋም ሳማና አሜከላ ይበቅሉባታል፤ የቀበሮም ማደሪያና የሰጐን ስፍራ ትሆናለች። የምድረ በዳም አራዊት ከተኩሎች ጋር ይገናኛሉ፣ አጋንንትም እርስ በርሳቸው ይጠራራሉ፤ ጅንም በዚያ ትኖራለች ለእርስዋም ማረፊያ ታገኛለች። በዚያም ዋሊያ ቤትዋን ትሠራለች እንቁላልም ትጥላለች ትቀፈቅፈውማለች ልጆችዋንም በጥላዋ ትሰበስባለች፤ በዚያም ደግሞ አሞራዎች እያንዳንዳቸው ከባልንጀሮቻቸው ጋር ይሰበሰባሉ።”​—⁠ኢሳይያስ 34:​10ለ-15a

      17 አዎን፣ ኤዶምያስ ባድማ ምድር ትሆናለች። አራዊት፣ አእዋፍና እባቦች ብቻ የሚኖሩባት የተተወች ምድር ትሆናለች። ይህ ደረቅ የሆነው የምድሪቱ ሁኔታ በ⁠ኢሳይያስ 34 ቁጥር 10 ላይ እንደተገለጸው “ለዘላለም ዓለም” ይቀጥላል። ተመልሳ የምትቋቋምበት መንገድ ፈጽሞ አይኖርም።​—⁠አብድዩ 18

  • ይሖዋ በብሔራት ላይ ቁጣውን ያፈስሳል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • a በሚልክያስ ዘመን ይህ ትንቢት ፍጻሜውን አግኝቶ ነበር። (ሚልክያስ 1:​3) ሚልክያስ ኤዶማውያን ባድማ በሆነችው ምድራቸው እንደገና ለመኖር ተስፋ አድርገው እንደነበር ዘግቧል። (ሚልክያስ 1:​4) ይሁን እንጂ ይሖዋ አልፈቀደም። እንዲያውም ከጊዜ በኋላ ሌላ ሕዝብ ማለትም ነባዮታውያን የኤዶምያስን ምድር ወርሰዋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ