የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ተመልሶ የተቋቋመ ገነት!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • የአዲስ ብሔር መወለድ

      19. በስድስተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ የኢሳይያስ ትንቢት ያገኘው ፍጻሜ ውስን ነበር የምንለው ለምንድን ነው?

      19 እርግጥ ኢሳይያስ ምዕራፍ 35 በስድስተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ ያገኘው ፍጻሜ ውስን ነበር። ወደ ምድራቸው የተመለሱት አይሁዳውያን በመንፈሳዊ መንገድ ያገኙት ገነታዊ ሁኔታ አልዘ​ለቀም። ከጊዜ በኋላ የሐሰት ሃይማኖታዊ ትምህርቶችና ብሔራዊ ስሜት ንጹሑን አምልኮ በክለዋል። በመንፈሳዊ ሁኔታ አይሁዳውያኑ ወደ ኃዘንና ትካዜ ተመልሰዋል። በመጨረሻም ይሖዋ እንደ ሕዝቡ አድርጎ መመልከቱን ተወ። (ማቴዎስ 21:​43) እንደገና በማመፃቸው ደስታቸው ሳይዘልቅ ቀርቷል። ይህ ሁሉ ደግሞ ኢሳይያስ ምዕራፍ 35 ሌላ ተጨማሪ ፍጻሜ እንዳለው የሚጠቁም ነው።

      20. በመጀመሪያው መቶ ዘመን እዘአ ብቅ ያለው አዲስ እስራኤል የትኛው ነው?

      20 ይሖዋ የወሰነው ጊዜ ሲደርስ ሌላ እስራኤል ማለትም መንፈሳዊ እስራኤል ወደ ሕልውና መጥቷል። (ገላትያ 6:​16) ኢየሱስ በምድር ባከናወነው አገልግሎት ወቅት ለዚህ አዲስ እስራኤል መወለድ ሁኔታውን አመቻችቷል። ንጹሕ አምልኮን መልሶ ያቋቋመ ሲሆን በትምህርቶቹ አማካኝነትም የእውነት ውኃ እንደገና መፍሰስ ጀምሯል። በአካላዊም ሆነ በመንፈሳዊ የታመሙትን ፈውሷል። የአምላክ መንግሥት ምሥራች ሲታወጅም የደስታ ዝማሬ ተሰምቷል። ሞቶ ትንሣኤ ካገኘ በኋላ ሰባት ሳምንታት ያህል ቆይቶ ክብር የተቀዳጀው ኢየሱስ የክርስቲያን ጉባኤን ማለትም በፈሰሰው የኢየሱስ ደም ተዋጅተው የአምላክ መንፈሳዊ ልጆችና የኢየሱስ ወንድሞች በመሆን በመንፈስ ቅዱስ ከተቀቡ አይሁዶችና ሌሎች ሰዎች የተውጣጣውን መንፈሳዊ እስራኤል አቋቁሟል።​—⁠ሥራ 2:​1-4፤ ሮሜ 8:​16, 17፤ 1 ጴጥሮስ 1:​18, 19

  • ተመልሶ የተቋቋመ ገነት!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 21. በመጀመሪያው መቶ ዘመን ከነበረው የክርስቲያን ጉባኤ ጋር በተያያዘ መንገድ የኢሳይያስ ትንቢት ፍጻሜ ናቸው ሊባሉ የሚችሉት ክንውኖች የትኞቹ ናቸው?

      21 ሐዋርያው ጳውሎስ የመንፈሳዊ እስራኤል አባላት ለሆኑት ሰዎች ሲጽፍ የ⁠ኢሳይያስ 35:​3ን ቃላት በመጥቀስ “የላሉትን እጆች የሰለሉትንም ጒልበቶች አቅኑ” ብሏል። (ዕብራውያን 12:​12) እንግዲያው በግልጽ ለመረዳት እንደሚቻለው የ⁠ኢሳይያስ ምዕራፍ 35 ቃላት በመጀመሪያው መቶ ዘመንም ተፈጻሚነት ነበራቸው። ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ ተዓምራዊ በሆነ መንገድ የዕውራን ዓይን እንዲያይ የደንቆሮዎች ጆሮ እንዲሰማ አድርገዋል። ‘አንካሶች’ በእግራቸው እንዲሄዱና መናገር የተሳናቸው እንዲናገሩ አድርገዋል። (ማቴዎስ 9:​32፤ 11:​5፤ ሉቃስ 10:​9) ከዚህ ይበልጥ ትርጉም ያለው ግን ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ከሐሰት ሃይማኖት ነፃ ወጥተው በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ በመንፈሳዊ ገነት መካከል ለመገኘት መብቃታቸው ነው። (ኢሳይያስ 52:​11፤ 2 ቆሮንቶስ 6:​17) ከባቢሎን እንደተመለሱት አይሁዳውያን ሁሉ ከሐሰት ሃይማኖት ያመለጡት እነዚህ ሰዎችም አዎንታዊ አመለካከትና የድፍረት መንፈስ ማሳየታቸው አስፈላጊ ነበር።​—⁠ሮሜ 12:​11

      22. ቅን ልብ ያላቸው እውነትን የሚፈልጉ ክርስቲያኖች በዘመናችን በባቢሎናዊ ምርኮ ተይዘው ነበር ሊባል የሚቻለው እንዴት ነው?

      22 ስለ ዘመናችንስ ምን ለማለት ይቻላል? የኢሳይያስ ትንቢት ዛሬ ያለውን የክርስቲያን ጉባኤ የሚመለከት የበለጠ ሰፊ ተፈጻሚነት ይኖረዋልን? አዎን፣ ይኖረዋል። ሐዋርያት ከሞቱ በኋላ የእውነተኛዎቹ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ቁጥር በእጅጉ ሲመናመን የሐሰት ክርስትና ማለትም ‘እንክርዳዱ’ ተንሠራፍቶ ብቅ ብሏል። (ማቴዎስ 13:​36-43፤ ሥራ 20:​30፤ 2 ጴጥሮስ 2:​1-3) ቅን ልብ ያላቸው ግለሰቦች ራሳቸውን ከሌሎች በመለየት እውነተኛውን አምልኮ ለማግኘት ይጣጣሩ በነበረበት በ19ኛው መቶ ዘመን እንኳ የነበራቸው እውቀት ቅዱስ ጽሑፋዊ ባልሆኑ ትምህርቶች የተበከለ ነበር። ኢየሱስ መሲሐዊ ንጉሥ ሆኖ በ1914 ቢሾምም ብዙም ሳይቆይ የታየው ሁኔታ እውነትን የሚፈልጉትን የእነዚህን ቅን ሰዎች ተስፋ ያጨለመው ይመስል ነበር። በትንቢት በተነገረው መሠረት አሕዛብ ‘ከእነርሱ ጋር ተዋግተው ስላሸነፏቸው’ እነዚህ ቅን ክርስቲያኖች ምሥራቹን ለመስበክ ያደረጉት የነበረው ጥረት ተስተጓጉሏል። በባቢሎን ምርኮ የተያዙ ያህል ሆነው ነበር።​—⁠ራእይ 11:​7, 8

      23, 24. ከ1919 ጀምሮ የኢሳይያስ ቃላት በአምላክ ሕዝብ መካከል ፍጻሜያቸውን ያገኙት በምን መንገዶች ነው?

      23 ይሁን እንጂ በ1919 ሁኔታዎች ተለወጡ። ይሖዋ ሕዝቡን ከምርኮ ነፃ አወጣቸው። ቀደም ሲል አምልኳቸውን በክለውባቸው የነበሩትን የሐሰት ትምህርቶች ማስወገድ ጀመሩ። ከዚህ የተነሳ ፈውስ አገኙ። ዛሬም ጭምር በምድር ዙሪያ እየተስፋፋ ባለው መንፈሳዊ ገነት ውስጥ ለመገኘት በቅተዋል። ለአምላክ ቅዱስ መንፈስ አሠራር ንቁ በመሆንና ዘወትር ወደ ይሖዋ ተጠግቶ መኖር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ በመገንዘብ በመንፈሳዊ ሁኔታ ዕውራን የነበሩት ማየት ችለዋል እንዲሁም ደንቆሮ የነበሩት መስማት ችለዋል። (1 ተሰሎንቄ 5:​6 NW፤ 2 ጢሞቴዎስ 4:​5 NW) አፋቸው የተፈታው ክርስቲያኖች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለሌሎች በማወጅ ‘ዝማሬያቸውን’ ለማሰማት ይጓጓሉ። (ሮሜ 1:​15 የ1980 ትርጉም) በመንፈሳዊ ደካማ ወይም “አንካሳ” የነበሩት ሰዎች አሁን ቀናተኞችና ደስተኞች ሆነዋል። በምሳሌያዊ አነጋገር ‘እንደ ሚዳቋ ይዘልላሉ።’

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ