-
“እባክህ ወደ ቤትህ መልሰን”መጠበቂያ ግንብ—2012 | ሚያዝያ 1
-
-
“በታላቅ ርኅራኄም እራራለታለሁ”
ይሖዋ ከእስራኤላውያን ጋር ልዩ ዝምድና ነበረው። “እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፣ ኤፍሬም በኵር ልጄ ነው” በማለት ተናግሯል። (ኤርምያስ 31:9) አንድ አፍቃሪ አባት፣ ልጁ ከልቡ ተጸጽቶ ቢመለስ እሱን ለመቀበል እምቢ ሊል ይችላል? ይሖዋም ለሕዝቡ ያለውን አባታዊ ፍቅር እንዴት እንደገለጸ ልብ በል።
“ኤፍሬም የምወደው፣ ደስም የምሰኝበት ልጄ አይደለምን? ብዙ ጊዜ ተቃውሜው ብናገርም፣ መልሼ ስለ እርሱ አስባለሁ።” (ቁጥር 20) ይህ ምንኛ ልብ የሚነካ አነጋገር ነው! ጥብቅ ሆኖም አፍቃሪ እንደሆነ አባት፣ አምላክ ከኃጢአታቸው እንዲመለሱ ልጆቹን በተደጋጋሚ በማስጠንቀቅ እነሱን ‘ተቃውሞ’ ለመናገር ተገድዶ ነበር። ልጆቹ እሱን ለመስማት አሻፈረን በማለታቸው በግዞት እንዲወሰዱ ሲፈቅድም ከቤቱ እንዲወጡ ያደረገ ያህል ነበር። ሆኖም አምላክ በዚህ መልኩ ቢቀጣቸውም ሕዝቡን አልረሳቸውም። ይህን ፈጽሞ ሊያደርግ አይችልም። አንድ አፍቃሪ አባት ልጆቹን አይረሳም። ታዲያ ይሖዋ ልጆቹ ከልባቸው ንስሐ እንደገቡ ሲመለከት ምን ተሰማው?
“አንጀቴ ይላወሳል፤b በታላቅ ርኅራኄም እራራለታለሁ።” (ቁጥር 20) ይሖዋ ልጆቹ እንዲመለሱ በጣም ይናፍቅ ነበር። እውነተኛ የንስሐ ዝንባሌ ማሳየታቸው ልቡን ነክቶታል፤ እንዲሁም ወደ እሱ የሚመለሱበትን ጊዜ በጉጉት ይጠባበቅ ነበር። በኢየሱስ ምሳሌ ላይ እንደተጠቀሰው የአባካኙ ልጅ አባት፣ ይሖዋም ስለ ልጆቹ ሲያስብ ‘አንጀቱ የሚላወስ’ ከመሆኑም ሌላ እነሱን ለመቀበል ይጓጓል።—ሉቃስ 15:20
‘ይሖዋ ወደ ቤቱ መለሰኝ!’
በኤርምያስ 31:18-20 ላይ የሚገኙት ቃላት ይሖዋ የሚያሳየውን ከልብ የመነጨ ርኅራኄና ምሕረት በጥልቀት እንድናስተውል ረድተውናል። አምላክ በአንድ ወቅት ያገለግሉት የነበሩ ሰዎችን አይረሳም። እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ወደ እሱ ለመመለስ ቢፈልጉስ? አምላክ “ይቅር ባይ” ነው። (መዝሙር 86:5) ከልብ ተጸጽተው ወደ እሱ የሚመለሱ ሰዎችን ፈጽሞ ችላ አይልም። (መዝሙር 51:17) እንዲያውም እነዚህ ሰዎች ወደ ቤቱ ሲመለሱ በደስታ ይቀበላቸዋል።—ሉቃስ 15:22-24
-
-
“እባክህ ወደ ቤትህ መልሰን”መጠበቂያ ግንብ—2012 | ሚያዝያ 1
-
-
b አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች መመሪያ ጽሑፍ ስለ አንጀት መላወስ የሚገልጸውን ሐሳብ በተመለከተ እንዲህ ይላል፦ “አይሁዳውያን ስሜታቸውን ለመግለጽ ውስጣዊ የአካላቸውን ክፍሎች ይጠቅሳሉ።”
-