የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ባሮክ የኤርምያስ ታማኝ ጸሐፊ
    መጠበቂያ ግንብ—2006 | ነሐሴ 15
    • “ታላቅ ነገር” አትፈልግ

      ባሮክ የመጀመሪያውን ጥቅልል በጻፈበት ወቅት ከመጨነቁ የተነሳ እንዲህ ብሎ ነበር:- “እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ሐዘን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ፤ ከልቅሶዬ ብዛት የተነሣ ደክሜያለሁ፤ ዕረፍትም የለኝም።” ሆኖም የጭንቀቱ መንስዔ ምን ነበር?—ኤርምያስ 45:1-3

      ይህን በተመለከተ ቀጥተኛ መልስ አናገኝም። ሆኖም ባሮክ የነበረበትን ሁኔታ በአእምሮህ ለመሳል ሞክር። ባሮክ፣ ለእስራኤልና ለይሁዳ ሕዝብ ለ23 ዓመታት ሲሰጥ የቆየውን ማስጠንቀቂያ እንደገና ሲናገር ሕዝቡ ከሃዲ መሆኑና ይሖዋን አንፈልግም ማለቱ ይበልጥ ግልጽ ሳይሆንለት አልቀረም። ይሖዋ ኢየሩሳሌምንና ይሁዳን አጥፍቶ ሕዝቡ ለ70 ዓመታት በግዞት ወደ ባቢሎን እንደሚወሰድ የተናገረው በዚያው ዓመት ሲሆን ምናልባትም ይህ ሐሳብ በጥቅልሉ ላይ ሰፍሮ ይሆናል፤ ይህም ባሮክን አስጨንቆት መሆን አለበት። (ኤርምያስ 25:1-11) ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ወሳኝ ጊዜ ኤርምያስን ጸንቶ መደገፉ ሥልጣኑንና ሥራውን ሊያሳጣው ይችላል።

      ያም ሆነ ይህ፣ ይሖዋ ራሱ ጣልቃ በመግባት ባሮክ ስለ መጪው ፍርድ እንዲያስታውስ ረድቶታል። ይሖዋ “በምድር ሁሉ የገነባሁትን አፈርሳለሁ፤ የተከልሁትን እነቅላለሁ” ሲል ነግሮታል። ከዚያም በመቀጠል “ታዲያ፣ ለራስህ ታላቅ ነገር ትሻለህን? . . . አትፈልገው” በማለት ባሮክን መክሮታል።—ኤርምያስ 45:4, 5

      ይሖዋ “ታላቅ ነገር” ብሎ የጠራው ምን እንደሆነ ለይቶ ባይነግረውም ይህ ነገር የራስ ወዳድነት ምኞት አሊያም ታዋቂ ለመሆን ወይም ቁሳዊ ብልጽግና ለማግኘት መፈለግ ሊሆን እንደሚችል ባሮክ ሳይገባው አይቀርም። ይሖዋ፣ ባሮክ ሐቁን እንዲቀበልና ከፊቱ ምን እንደሚጠብቀው እንዲገነዘብ ለማድረግ እንዲህ በማለት መክሮታል:- “በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ጥፋት አመጣለሁና . . . ነገር ግን በሄድህበት ሁሉ ሕይወትህ እንዲተርፍልህ አደርጋለሁ።” ባሮክ የትም ቢሄድ ውድ የሆነው ንብረቱ ማለትም ሕይወቱ ይተርፍለታል።—ኤርምያስ 45:5

  • ባሮክ የኤርምያስ ታማኝ ጸሐፊ
    መጠበቂያ ግንብ—2006 | ነሐሴ 15
    • ይሁዳ ልትጠፋ አካባቢ ባሮክ ለራሱ “ታላቅ ነገር” የሚፈልግበት ጊዜ እንዳልሆነ በተነገረው ጊዜ ምክሩን በታዛዥነት ተቀብሎ መሆን አለበት፤ እንዲህ እንድንል ምክንያት የሚሆነን ሕይወቱ መትረፉ ነው። እኛም ዛሬ በዚህ ሥርዓት የመጨረሻ ጊዜ ውስጥ ስለምንገኝ ይህንን ምክር በሕይወታችን ተግባራዊ ማድረጋችን ምክንያታዊ ነው። ይሖዋም በተመሳሳይ ሕይወታችንን እንደሚያተርፍልን ቃል ገብቶልናል። ታዲያ እኛስ ባሮክ እንዳደረገው እንዲህ ላሉት ማሳሰቢያዎች አዎንታዊ ምላሽ መስጠት እንችላለን?

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ