የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከአምላክ ጋር ትሄዳለህ?
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | ኅዳር 1
    • 11. ይሖዋ በኤርምያስ 6:16 ላይ የሕዝቡን ልብ የሚነካ ምን ምሳሌያዊ አነጋገር ተጠቅሟል? ይሁንና ምላሻቸው ምን ነበር?

      11 የአምላክ ቃል ያን ያህል በቅርብ ሆኖ እንዲመራን በእርግጥ ፈቅደናል? አንዳንድ ጊዜ ቆም ብለን በታማኝነት ራሳችንን መመርመሩ ጠቃሚ ነው። እንዲህ እንድናደርግ የሚረዳንን አንድ ጥቅስ ተመልከት:- “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘መንታ መንገድ ላይ ቁሙ፣ ተመልከቱም፤ መልካሟን፣ የጥንቷን መንገድ ጠይቁ፤ በእርሷም ላይ ሂዱ። ለነፍሳችሁ ዕረፍት ታገኛላችሁ።’” (ኤርምያስ 6:16) እነዚህ ቃላት በመስቀለኛ መንገድ ላይ ቆሞ አቅጣጫ እየጠየቀ ያለን ተጓዥ አስታውሰውን ይሆናል። በእስራኤል የሚኖሩ በይሖዋ ላይ ያመጹ ሰዎች በመንፈሳዊ ሁኔታ ከተጓዡ ጋር የሚመሳሰል ነገር ማድረግ ያስፈልጋቸው ነበር። ተመልሰው “የጥንቷን መንገድ” መፈለግ ነበረባቸው። ‘መልካሟ መንገድ’ የተባለችው ታማኝ ቅድመ አያቶቻቸው ሲጓዙባት የነበረችውና ብሔሩ በሞኝነት የተዋት መንገድ ነች። የሚያሳዝነው እስራኤላውያን ይሖዋ የሰጠውን ፍቅራዊ ማሳሰቢያ ለመቀበል አሻፈረን አሉ። በዚያው ቁጥር ላይ “እናንተ ግን፣ ‘በእርሷ አንሄድም’ አላችሁ” የሚል ሐሳብ ይገኛል። ይሁን እንጂ በዘመናችን ያሉ የአምላክ ሕዝቦች እንዲህ ላለው ምክር ከዚህ የተለየ ምላሽ ሰጥተዋል።

      12, 13. (ሀ) የክርስቶስ ቅቡዓን ተከታዮች በኤርምያስ 6:16 ላይ ለተሰጠው ምክር ምላሽ የሰጡት እንዴት ነው? (ለ) በዛሬው ጊዜ እየሄድንበት ስላለው መንገድ ራሳችንን መመርመር የምንችለው እንዴት ነው?

      12 ከ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ጀምሮ የክርስቶስ ቅቡዓን ተከታዮች በኤርምያስ 6:16 ላይ የሚገኘው ምክር ለእነርሱ እንደሚሠራ ተሰምቷቸው ነበር። እነዚህ ቅቡዓን በቡድን ደረጃ በሙሉ ልባቸው ወደ ‘ጥንቷ መንገድ’ ተመልሰዋል። ከከሃዲዋ ሕዝበ ክርስትና በተቃራኒ ኢየሱስ ክርስቶስ የመሠረተውንና የመጀመሪያው መቶ ዘመን ታማኝ ተከታዮቹ የደገፉትን “የጤናማ ትምህርት ምሳሌ” የሙጥኝ ብለዋል። (2 ጢሞቴዎስ 1:13) እስከ አሁን ድረስ ቅቡዓኑ እርስ በርሳቸውና አጋሮቻቸው ከሆኑት “ሌሎች በጎች” ጋር እየተደጋገፉ ሕዝበ ክርስትና የተወችውን ጤናማና አስደሳች የሕይወት ጎዳና ይከተላሉ።—ዮሐንስ 10:16

      13 የታማኙ ባሪያ ክፍል መንፈሳዊ ‘ምግብ በጊዜው’ በማቅረብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች “የጥንቷን መንገድ” እንዲያገኙና ከአምላክ ጋር እንዲጓዙ እየረዳ ነው። (ማቴዎስ 24:45-47 የ1954 ትርጉም) አንተስ ከእነዚህ መካከል ትገኛለህ? ከሆነ ትክክለኛውን አቅጣጫ ስተህ የራስህን መንገድ እንዳትከተል ምን ማድረግ ትችላለህ? በየጊዜው ቆም እያልክ የሕይወት አቅጣጫህን መመርመርህ መልካም ነው። መጽሐፍ ቅዱስንና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ጽሑፎችን አዘውትረህ ካነበብክ እንዲሁም በዛሬው ጊዜ የሚገኙት ቅቡዓን በሚያዘጋጅዋቸው መመሪያ የሚሰጥባቸው ፕሮግራሞች ላይ ከተካፈልህ ከአምላክ ጋር ለመሄድ የሚያስችልህን ሥልጠና እያገኘህ ነው። በተጨማሪም የተሰጠህን ምክር በትሕትና ሥራ ላይ የምታውል ከሆነ “የጥንቷን መንገድ” ተከትለህ ከአምላክ ጋር እየሄድክ ነው።

  • ከአምላክ ጋር ትሄዳለህ?
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | ኅዳር 1
    • ምን በረከት እናገኛለን?

      17. በይሖዋ መንገድ ከሄድን ለነፍሳችን ምን ዓይነት “ዕረፍት” እናገኛለን?

      17 ከይሖዋ አምላክ ጋር መሄድ በረከት የሞላበት ሕይወት ያስገኛል። ይሖዋ ሕዝቡ ‘መልካሟን መንገድ’ ቢከተል የሚያገኘው ነገር እንዳለ ቃል እንደገባ አስታውስ። “በእርሷም ላይ ሂዱ። ለነፍሳችሁ ዕረፍት ታገኛላችሁ” ብሏቸው ነበር። (ኤርምያስ 6:16) እዚህ ላይ “ዕረፍት” የተባለው ምንድን ነው? ደስታና ቅንጦት የሞላበት ኑሮ ማለት ነው? አይደለም። ይሖዋ ከዚህ እጅግ የሚበልጥና የዓለም ሀብታሞች እምብዛም የማያገኙት ነገር ይሰጣል። ለነፍስህ እረፍት የምታገኘው ውስጣዊ ሰላም፣ ደስታና እርካታ ሲኖርህ እንዲሁም መንፈሳዊ ፍላጎትህ ሲሟላ ነው። እንዲህ ዓይነት እረፍት አለህ ማለት በሕይወት ጎዳና ላይ ጥሩውን መንገድ እንደመረጥክ ትተማመናለህ ማለት ነው። በዚህ አስቸጋሪ ዓለም ውስጥ እንዲህ ያለውን የአእምሮ ሰላም ማግኘት ደግሞ ትልቅ በረከት ነው!

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ