የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • እንደ ኤርምያስ በንቃት ተጠባበቁ
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | መጋቢት 15
    • 10. ቅቡዓን ቀሪዎች “በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ” ተሹመዋል የምንለው ለምንድን ነው?

      10 “የሕዝቦች ሁሉ ንጉሥ” የሆነው ይሖዋ በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ የፍርድ መልእክት እንዲናገር ኤርምያስን ልኮት ነበር። (ኤር. 10:6, 7) ቅቡዓን ቀሪዎች “በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ” የተሾሙት በምን መንገድ ነው? (ኤር. 1:10) በጥንት ጊዜ እንደነበረው ነቢይ በዛሬው ጊዜ የሚገኘው የኤርምያስ ክፍልም ከጽንፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ገዥ ተልእኮ ተቀብሏል። በመሆኑም የተቀቡት የአምላክ አገልጋዮች በዓለም ዙሪያ ለሚገኙት አሕዛብና መንግሥታት አዋጅ እንዲናገሩ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል። የኤርምያስ ክፍል፣ ከሉዓላዊው አምላክ ባገኘው ሥልጣንና በመንፈስ መሪነት በተጻፈው ቃሉ ውስጥ በሚገኘው ግልጽ የሆነ መልእክት በመጠቀም ዛሬ ያሉት አሕዛብና መንግሥታት አምላክ በወሰነው ጊዜና እሱ በመረጠው መንገድ ተነቅለው እንደሚጣሉ ብሎም እንደሚጠፉ እያወጀ ነው። (ኤር. 18:7-10፤ ራእይ 11:18) የኤርምያስ ክፍል በምድር ዙሪያ የይሖዋን የፍርድ መልእክት እንዲያውጅ አምላክ የሰጠውን ተልእኮ ከመፈጸም ወደኋላ ላለማለት ቆርጧል።

  • እንደ ኤርምያስ በንቃት ተጠባበቁ
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | መጋቢት 15
    • 14, 15. (ሀ) ኤርምያስ እስከ መጨረሻው ድረስ ተልእኮውን በታማኝነት መወጣቱ ምን ፍሬ አስገኝቶለታል? (ለ) በዛሬው ጊዜ የአምላክ ሕዝቦች ከስብከቱ ሥራ ጋር በተያያዘ የትኛውን ሐቅ ይገነዘባሉ?

      14 ኤርምያስ የይሖዋን የማስጠንቀቂያና የፍርድ መልእክት ያለማሰለስ አውጇል፤ ያም ሆኖ ‘እንዲያንጽና እንዲተክል’ የተሰጠውን ተልእኮም አልዘነጋም። (ኤር. 1:10) የማነጽና የመትከል ሥራው ፍሬ አፍርቷል። በ607 ዓ.ዓ. ኢየሩሳሌም ስትጠፋ አንዳንድ አይሁዳውያንና እስራኤላውያን ያልሆኑ ሰዎች በሕይወት ተርፈዋል። ሬካባውያን፣ አቤሜሌክና ባሮክ ከጥፋቱ እንደተረፉ እናውቃለን። (ኤር. 35:19፤ 39:15-18፤ 43:5-7) ታማኝ የነበሩትና አምላክን የሚፈሩት እነዚህ የኤርምያስ ወዳጆች በዛሬው ጊዜ ምድራዊ ተስፋ ያላቸውንና የኤርምያስ ክፍል አጋር የሆኑትን ክርስቲያኖች ያመለክታሉ። የኤርምያስ ክፍል አባላት ይህን “እጅግ ብዙ ሕዝብ” በመንፈሳዊ መገንባት ታላቅ ደስታ አምጥቶላቸዋል። (ራእይ 7:9) በተመሳሳይም የቅቡዓን አጋሮች የሆኑት እነዚህ ታማኝ ክርስቲያኖች ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች እውነትን እንዲያውቁ መርዳት ጥልቅ እርካታ ያስገኝላቸዋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ