የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ነፍስህ እኔን ለመርዳት ታጎነብሳለች’
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ሰኔ 1
    • ትሕትና ተወዳጅ ባሕርይ ነው። ብዙውን ጊዜ ትሑት የሆኑ ሰዎች ይማርኩናል። የሚያሳዝነው ግን በዛሬው ጊዜ እውነተኛ ትሕትና የሚያሳዩ ሰዎች ማግኘት አስቸጋሪ ነው፤ በተለይም ሥልጣን ወይም የኃላፊነት ቦታ ያላቸው ሰዎች ይህን ባሕርይ ማሳየት ይከብዳቸዋል። በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ከሁሉ የበለጠ ኃያል የሆነው ይሖዋ አምላክስ ትሑት ነው? በ⁠ሰቆቃወ ኤርምያስ 3:20, 21 (NW) ላይ ነቢዩ ኤርምያስ የተናገረውን ሐሳብ እስቲ እንመርምር።​—ጥቅሱን አንብብ።a

  • ‘ነፍስህ እኔን ለመርዳት ታጎነብሳለች’
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | ሰኔ 1
    • ይሖዋ ከልባቸው ንስሐ የገቡ ሰዎችን ‘ለመርዳት እንደሚያጎነብስ’ ኤርምያስ እርግጠኛ ነበር። አንድ ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ይህን ጥቅስ “አስታውሰኝ፤ ወደ እኔም አዘንብል” በማለት አስቀምጦታል። እነዚህ ቃላት ይሖዋ ምን ያህል ደግ እና ገር እንደሆነ በዓይነ ሕሊናችን እንድንስል ይረዱናል። “በምድር ሁሉ ላይ . . . ልዑል” የሆነው ይሖዋ በምሳሌያዊ አነጋገር ጎንበስ በማለት አምላኪዎቹን ከወደቁበት የውርደት አዘቅት አውጥቶ እንደገና ሞገሱን ያሳያቸዋል። (መዝሙር 83:18) ኤርምያስ እንዲህ ዓይነት ተስፋ ስላለው በሐዘን የተደቆሰው ልቡ ሊጽናና ችሏል። ይህ ታማኝ ነቢይ፣ ይሖዋ ንስሐ የገቡትን ሰዎች ለማዳን የወሰነው ጊዜ እስኪደርስ በትዕግሥት ለመጠባበቅ ቆርጦ ነበር።​—ቁጥር 21

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ