-
“የሚሠሯቸውን ክፉና አስጸያፊ ነገሮች ተመልከት”የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
ሦስተኛ ትእይንት፦ ‘ሴቶች ታሙዝ ለተባለው አምላክ ያለቅሳሉ’
13. ሕዝቅኤል በሰሜን በኩል ባለው የቤተ መቅደሱ በር ላይ ከሃዲ የሆኑ ሴቶች ምን ሲያደርጉ ተመለከተ?
13 ሕዝቅኤል 8:13, 14ን አንብብ። ሕዝቅኤል አስጸያፊ ድርጊት ሲፈጸም የሚያሳዩትን ሁለት ትእይንቶች ከተመለከተ በኋላ ይሖዋ “እነሱ የሚሠሯቸውን ይበልጥ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮች ታያለህ” አለው። ታዲያ ነቢዩ ቀጥሎ ምን ይመለከት ይሆን? ‘በሰሜን በኩል ባለው የይሖዋ ቤት በር’ “ሴቶች ተቀምጠው ታሙዝ ለተባለው አምላክ ሲያለቅሱ” አየ። የሜሶጶጣሚያ አምላክ የሆነው ታሙዝ በሱሜሪያ ጽሑፍ ላይ ዱሙዚ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን የመራባት እንስት አምላክ የሆነችው የኢሽታር ፍቅረኛ እንደሆነ ይታሰባል።d እስራኤላውያኑ ሴቶች የሚያለቅሱት ከታሙዝ ሞት ጋር ተያያዥነት ያለው ሃይማኖታዊ ሥርዓት ለመፈጸም ሳይሆን አይቀርም። እነዚህ ሴቶች በይሖዋ መቅደስ ውስጥ ለታሙዝ በማልቀስ የንጹሕ አምልኮ ማዕከል በሆነው ቦታ ላይ አረማዊ አምልኮ እያካሄዱ ነበር። ይሁን እንጂ የሐሰት አምልኮ በአምላክ ቤተ መቅደስ ውስጥ ስለተከናወነ ብቻ የተቀደሰ ሊሆን አይችልም። እነዚህ ከሃዲ ሴቶች የሚያከናውኑት ነገር በይሖዋ ዓይን “አስጸያፊ” ነበር።
14. ይሖዋ ከሃዲዎቹ ሴቶች ለፈጸሙት ድርጊት የነበረውን አመለካከት ማወቃችን ምን ያስተምረናል?
14 ይሖዋ እነዚህ ሴቶች ለፈጸሙት ድርጊት የነበረውን አመለካከት ማወቃችን ምን ያስተምረናል? አምልኳችን ንጹሕ እንዲሆን ከፈለግን ንጹሑን አምልኮ ርኩስ ከሆኑ አረማዊ ልማዶች ጋር ፈጽሞ መቀላቀል አይኖርብንም። በመሆኑም አረማዊ ምንጭ ካላቸው ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት ሙሉ በሙሉ መራቅ ይገባናል። አንድ ክብረ በዓል የመነጨው ከየት ነው የሚለው ጉዳይ ለውጥ ያመጣል? አዎ! ለምሳሌ እንደ ገና እና በዓለ ትንሣኤ ካሉት በዓላት ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ልማዶች ምንም ጉዳት የሌላቸው ሊመስሉ ይችላሉ። ይሁንና ይሖዋ በዛሬው ጊዜ ከሚከናወኑ ሃይማኖታዊ በዓላት ጋር የተቀላቀሉትን አረማዊ ልማዶች ከጅምሩ አንስቶ እንደተመለከተ ልንዘነጋ አይገባም። ረጅም ዘመን ማለፉ ወይም እነዚህን ልማዶች ከንጹሕ አምልኮ ጋር ለመቀላቀል ጥረት መደረጉ ይሖዋ ለአረማዊ ልማዶች ያለውን አመለካከት አያለዝበውም።—2 ቆሮ. 6:17፤ ራእይ 18:2, 4
-