-
‘በግንባራቸው ላይ ምልክት አድርግ’የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
5, 6. ምልክት የተደረገባቸውን ሰዎች በተመለከተ ምን ማለት ይቻላል? (በመግቢያው ላይ ያለውን ሥዕል ተመልከት።)
5 የቀለም ቀንድ የያዘው ሰው የሚያከናውነው ሥራ ምንድን ነው? ይሖዋ ራሱ የሚከተለውን ከባድ ተልእኮ ሰጠው፦ “በከተማዋ መካከል ይኸውም በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፤ በከተማዋ ውስጥ እየተፈጸሙ ባሉት አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ እያዘኑና እየቃተቱ ባሉት ሰዎች ግንባር ላይም ምልክት አድርግ።” ምናልባትም ሕዝቅኤል ይህን ሲሰማ በጥንት ጊዜ የበኩር ልጆቻቸው ከጥፋት እንዲተርፉ በበራቸው ጉበንና መቃኖች ላይ የደም ምልክት ያደረጉትን ታማኝ እስራኤላውያን ወላጆች አስታውሶ ይሆናል። (ዘፀ. 12:7, 22, 23) በሕዝቅኤል ራእይ ላይ የቀለም ቀንድ የያዘው ሰው በሰዎቹ ግንባር ላይ የሚያደርገው ምልክትስ ሰዎቹ ከኢየሩሳሌም ጥፋት የሚተርፉ መሆኑን የሚያመለክት ይሆን?
6 የዚህን ጥያቄ መልስ ለማግኘት ምልክት የሚደረግባቸው ምን ዓይነት ሰዎች እንደሆኑ መመልከት ይኖርብናል። ምልክቱ የሚደረገው “በከተማዋ ውስጥ እየተፈጸሙ ባሉት” አስጸያፊ ነገሮች “እያዘኑና እየቃተቱ” ባሉት ሰዎች ግንባር ላይ ነው። እንግዲያው ምልክት የተደረገባቸውን ሰዎች በተመለከተ ምን ማለት ይቻላል? አንደኛ ነገር፣ እነዚህ ሰዎች ከልባቸው ያዘኑት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ይፈጸም በነበረው ጣዖት አምልኮ ምክንያት ብቻ ሳይሆን ኢየሩሳሌምን በሞላው ዓመፅ፣ የሥነ ምግባር ብልግናና ምግባረ ብልሹነት ጭምር ነው። (ሕዝ. 22:9-12) በተጨማሪም ሰዎቹ የተሰማቸውን ሐዘን በውስጣቸው ብቻ ይዘው የነበረ አይመስልም። ቅን ልብ ያላቸው እነዚህ ሰዎች በምድሪቱ ይፈጸሙ በነበሩት ነገሮች ምክንያት የተሰማቸውን ሐዘንና ለንጹሕ አምልኮ ያላቸውን ታማኝነት በንግግራቸውም ሆነ በድርጊታቸው በግልጽ አሳይተው መሆን አለበት። መሐሪ አምላክ የሆነው ይሖዋ መትረፍ የሚገባቸውን እነዚህን ሰዎች ከጥፋቱ ያድናቸዋል።
-
-
‘በግንባራቸው ላይ ምልክት አድርግ’የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
-
-
9, 10. ከኢየሩሳሌም ጥፋት ከዳኑት ታማኝ ሰዎች መካከል እነማን ይገኙበታል? እነዚህን ሰዎች በተመለከተስ ምን ማለት ይቻላል?
9 ሁለተኛ ዜና መዋዕል 36:17-20ን አንብብ። የሕዝቅኤል ትንቢት ፍጻሜውን ያገኘው በ607 ዓ.ዓ. የባቢሎን ሠራዊት ኢየሩሳሌምንና ቤተ መቅደሷን ባጠፋበት ጊዜ ነበር። ይሖዋ ‘በእጁ እንዳለ ጽዋ’ የሆኑትን ባቢሎናውያንን ተጠቅሞ በከዳተኛይቱ ኢየሩሳሌም ላይ ቁጣውን በማፍሰስ የቅጣት ፍርዱን አስፈጸመ። (ኤር. 51:7) ጥፋቱ ጅምላ ጨራሽ ነበር? በፍጹም። ሕዝቅኤል ባየው ራእይ ላይ በባቢሎናውያን የማይገደሉ ሰዎች እንደሚኖሩ ተገልጿል።—ዘፍ. 18:22-33፤ 2 ጴጥ. 2:9
10 ሬካባውያንን፣ ኢትዮጵያዊው ኤቤድሜሌክን፣ ነቢዩ ኤርምያስንና ጸሐፊው ባሮክን ጨምሮ የተወሰኑ ታማኝ ሰዎች ከጥፋቱ ተርፈዋል። (ኤር. 35:1-19፤ 39:15-18፤ 45:1-5) እነዚህ ሰዎች በኢየሩሳሌም ውስጥ ‘እየተፈጸሙ ባሉት አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ያዝኑና ይቃትቱ’ እንደነበር ሕዝቅኤል ያየው ራእይ ይጠቁማል። (ሕዝ. 9:4) ገና ጥፋቱ ከመድረሱ በፊት፣ ለክፋት ያላቸውን ልባዊ ጥላቻና ለንጹሕ አምልኮ ያላቸውን ታማኝነት እንዳሳዩ ምንም ጥያቄ የለውም፤ በዚህም ምክንያት ከጥፋቱ ለመትረፍ በቅተዋል።
11. የማጥፊያ መሣሪያ የያዙት ስድስት ሰዎችና የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘው ሰው እነማንን ይወክላሉ?
11 እነዚህ ታማኝ ሰዎች ከጥፋት ለመትረፍ የሚያስችል ምልክት ቃል በቃል ተደርጎባቸው ነበር? ሕዝቅኤልም ሆነ ሌላ ማንም ነቢይ በኢየሩሳሌም ከተማ እየተዘዋወረ በታማኝ ሰዎች ግንባር ላይ ምልክት እንዳደረገ የሚገልጽ ታሪክ የለም። በመሆኑም የሕዝቅኤል ትንቢታዊ ራእይ የሚያሳየው ከሰብዓዊ ዓይን እይታ ውጭ በሆነው በመንፈሳዊው ዓለም ይከናወን የነበረውን ነገር መሆን አለበት። በራእዩ ላይ የታዩት የማጥፊያ መሣሪያ የያዙ ስድስት ሰዎችና የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘው ሰው፣ ምንጊዜም የይሖዋን ፈቃድ ለመፈጸም በተጠንቀቅ የሚጠብቁትን ታማኝ መንፈሳዊ ፍጡራን ይወክላሉ። (መዝ. 103:20, 21) ይሖዋ በከሃዲዋ ኢየሩሳሌም ላይ የተወሰደውን የፍርድ እርምጃ ለመምራት በመላእክቱ ተጠቅሞ እንደነበረ አያጠራጥርም። መላእክቱ ፍርዱ ጅምላ ጨራሽ ሳይሆን ጥፋት የሚገባቸውን ብቻ መርጦ የሚያጠፋ እንዲሆን አድርገዋል፤ በዚህ መንገድ ከጥፋቱ በሚተርፉት ሰዎች ግንባር ላይ ምልክት እንዳደረጉ ሊቆጠር ይችላል።
-